መነሻ ገጽ አፍሪካ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የሚያቆመው ጠፍቷል !!
አፍሪካአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግኢትዮጵያ ንግድ ባንክዜናዎች

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የሚያቆመው ጠፍቷል !!

አጋራ
አጋራ

በግብፅ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣርያውን እያካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ በምድቡ የመጨረሻ ሶስተኛ ጨዋታ ተጋጣሚዉን ዩይ ጆይንት ስታር ከማራኪ የጨዋታ ብልጫ ጋር 10ለ0 አሸንፋል።

በተመሳሳይ አስር ጎሎችን አስቆጥረው ካሸነፉበት የኒዉ ጄኔሬሽን ጨዋታ የስድስት ተጫዋቾችን ለዉጥ አድርገዉ ወደ ሜዳ የገቡት ንግድ ባንኮች በካሳራኒ ስታዲየም ባደረጉት የምድቡ ሶስተኛ ጨዋታም ተጋጣሚያቸው ዩይ ጆይንት ስታር ላይ ጎሎችን ማዝነባቸዉን ቀጥለዉበታል።

በጨዋታዉም አምበሏ ሎዛ አበራ ስድስት ጎሎችን ስታስቆጥር በውድድሩም ያስቆጠረቻቸውን የግብ መጠን ወደ አስራ ሁለት ከፍ አድርጋለች። ቀሪዎቹን የንግድ ባንክ ጎሎች መዲና አዎል እና ፀጋነሽ ወልደየሱስ እያንዳንዳቸው ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችለዋል።

ንግድ ባንክ በሶስት ጨዋታዎች በተጋጣሚዎቻቸው ላይ ሀያ አራት ጎሎችን ከመረብ ማሰረፍ የቻሉ ሲሆን ፤ ምድባቸውንም በበላይነት በማጠናቀቅ ግማሽ ፍፃሜውን ለመቀላቀል ችለዋል።

በተያያዘም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጣይ ሰኞ ከዩጋንዳው ሌዲ ዶቭ ጋር ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል። ንግድ ባንክ ሰኞ ድል የሚቀናቸው ከሆነ ምስራቅ አፍሪካን በመወከል በግብፅ በህዳር ወር 2014 ላይ ለሚካሄደው አሁጉራዊ የመጨረሻ ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...