በግብፅ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የአፍሪካ ሴቶች ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ ለመሳተፍ የቀጠናውን የማጣሪያ ውድድር በኬንያ እያደረጉ የሚገኙት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በዛሬው ዕለት ሁለተኛ የምድብ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።
በመጀመሪያው የምድብ ጨዋታ ቪጋ ኪውንስን አራት ለሁለት ማሸነፍ የቻሉት ባንኮች በዛሬዉ ዕለት የምድቡን ሁለተኛ ጨዋታ ከቀኑ 7:00 ላይ ከኒዉ ጀኔሬሽን ጋር በካሳራኒ ስታዲየም የሚያደርጉም ይሆናል።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ተጋጣሚያቸዉን የሚያሸንፉ ከሆነም ቀሪ አንድ የምድብ ጨዋታ እያላቸዉ አስቀድመዉ ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፋቸውን የሚያረጋግጡ ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ