መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

አጋራ
አጋራ

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ ቀናችን እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ
አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን ይዘናል

በሀገር ውስጥ ዘገባችን ከ130-150 ሺህ የተጣራ ወርሃዊ ደመወዝ እየቀረበለትም እንቢ ብሎ ፊቱን አዙሯል ባለፉት ሁለት አመታት ለቡናማዎቹ ለመፈረም ፈልጎ አልተሳካለትም ..ዘንድሮ ግን ካሳዬ አራጌ ደወለለትና አናገረው.. በ100ሺህ ብር ወርሃዊ ደመወዝ ኢትዮዽያ ቡናን ለቀጣዮቹ 3 አመታት ለማገልገል ፊርማውን ያኖረው ነስረዲን ሃይሉ እንግዳችን ነው… ከዮሴፍ ከፈለኝ ጋር ያወጋው ነስረዲን “ኢትዮዽያ ቡናና ካሳዬን ወድጄ መርጬና ፈቅጄ ነው የመጣሁት” ሲልም በሙሉ ልብነት ተናግሯል።

*….የቅርቦቹ ሳምንታቶች ላይ የተጨዋቾች የትዳር መመስረት ዜናዎችን እየሰማን ነው የሀትሪኩ ይስሃቅ በላይ በዚህ የህይወት ቁምነገር ዙሪያ ያዘጋጀውን መረጃም ይዘናል…

*… “የኢትዮዽያ ቡና የስራ ኣመራር ቦርድ የቆረጠ ይመስላል… ካሳዬ አራጌ በአስቸኳይ ወደ ሰራ ገበታው እንዲመለስ አዟል…አሰልጣኙ ግን “ምክትል አሰልጣኜ ዘላለም ጸጋዬ አብሮኝ ከሌለ አልሄድም” ያለ ይመስላል…. መጪው ጊዜ ለቡና ወሳኝ ነው….

*……. ከባህርዳር ከተማ ወደ ወላይታ ድቻ ያቀናው ምንይሉ ወንድሙ “በወላይታ ድቻ የቀድሞ ስምና ዝናዬን እንደምመልስ ርግጠኛ ነኝ” ሲል የወልቂጤ ከተማው አብዱልከሪም ወርቁ በበኩሉ”አዲስ ነገር ካልተፈጠረ በስተቀር ከወልቂጤ ከተማ ጋር እቀጥላለሁ” ብሏል..ሁለቱንም መሸሻ ወልዴ አነጋግሯቸዋል።

*…..በውጪ ሃገር ዘገባዎቻችን….

*….ሊዮኔል ሜሲ ከ21 አመታት ቆይታ በኋላ ባርሴሎና እንደሚለቅ ተረጋግጧል… በዚህ ዙሪያ መረጃ ይዘናል…..

*….. መድፈኞቹን የተቀላቀለው ቤን ዋይት “በስተመጨረሻ ህልሜ እውን ሆኗል” ሲል ወደ ኤምሬትስ ያደረገው ን ጉዞ አወድሷል…..

*…… ማን.ዩናይትድ የሪያል ማድሪዱን የመሃል ተከላካይ ራፋኤል ቫራንን አስፈርሟል.. ማን.ዩናይትድን ለዋንጫ ድል ያበቃው ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው..በዝውውሩ ዙሪያ የተዘጋጀ ዘገባን አካተናል…..

*…. በሊቨርፑል የሚያቆየውን ኮንትራት የፈረመው ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ “በሊቨርፑል ህልሞቼን በሙሉ እውን ማድረግ ችያለሁ” ሲል ተናግሯል።

*… በጉዳት ለረጅም ጊዜ ተገልሎ የነበረውና አገግሞ ወደ ውደድር የተመለሰው ቨርጂል ቫንዳይክም የተናገረውን አካተናል።

*…የአስቶን ቪላው ኮከብ ጃክ ግሪሊሽ በእንግሊዝ የዝውውር ሪከርድ በሆነ መቶ ሚሊዮን ፓውንድ ከቪላፓርክ ወደ ኢትሃድ አቅንቷል….በዚህ ዙሪያ የሚያጠነጥን መረጃም አካተናል….

እናም ሌሎች መረጃዎች….

እርስዎ ብቻ ቀጠሯችንን አክብረው ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ ተዝናንተው ቁምነገር የሚጨብጡበት አዳዲስ መረጃዎችንን የሚያገኙበት ይሆናል…..

ቅዳሜና እሁዳችሁ
የተባረከ ይሁን……

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...