በዝዉዉር መስኮቱ በርካታ የሚባሉ ተጨዋቾችን ከቡድናቸዉ የለቀቁት ሰበታ ከተማዎች እነርሱን ለመተካት እና ስብስባቸዉን ለማጠናከር ይረዳቸዉ ዘንድ የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
በትላንትናው ዕለት በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ የቀላቀሉት ሰበታዎች በተጨማሪም ተከላካዩን ወ/አማኑኤል ጌቱን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ማስፈረማቸዉም ታዉቋል።
ረዘም ላሉ አመታት በጥሩ ብቃት በመጫወት ለክለቡ ለኢትዮ ኤሌትሪክ ግልጋሎትን ሲሰጥ የቆየዉ ተጫዋቹ አሁን ደግሞ ወደ ሰበታ ከተማ ማምራቱ እርግጥ ሆኖአል። ከቀጣዩ የዉድድር አመት አንስቶም ለሶስት አመታት በሰበታ መለያ የምንመለከተው ይሆናል።
አስተያየት ይስጡ