የታገደው ክለብ ዝውውር እያደረገ መሆኑ የህጋዊነት ጥያቄ ተነስቶበታል
ከደረቅ ቼክ ጋር ተያይዞ ከቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ውስጥ የዋሉት የሀድያ ሆሳዕናው የፋይናንስ ሃላፊ ከተከሰሱበት 11 ክሶች በ2ኛው ክስ ለሃምሌ 20 ተቀጠሩ።
ሃላፊው ለ15 ተጨዋቾች የደረቅ ቼክ ሰጥተዋል በሚል በ11 ክስ ተከሰው ባለፈው ሃሙስ አዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው በአንዱ ተጨዋች የ120 ሺህ ብር ክስ በ4 ሺ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ቢወሰንም በ10ሩ ክስ ወደ ማረፊያ ቤት እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል።
ከትላንት ቢስቲያም በተስፋዬ በቀለ /ጃምቦ/ መዝገብ ተከሰው ፍ/ቤት የቀረቡ ሲሆን ለሃምሌ 20/2013 ተቀጥረው ወደ ማረፊያ ቤት ተመልሰዋል።
በተመሳሳይ ክስ የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ማዶሮ በፖሊስ እየተፈለጉ ቢሆንም እስካሁን እጃቸውን አለመስጠታቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል እገዳ ላይ ያለው ሀድያ ሆሳእና ተጨዋቾችን እያስፈረመ መሆኑ የህጋዊነት ጥያቄ አስነስቷል።
የአዲሱ አሰልጣኝ ሙሉጌታ ምህረት ውል ባልጸደቀበትና ክለቡ በታገደበት ሁኔታ ተጨዋቾችን እያዘዋወረ መሆኑ ጥያቄ ተነስቷል። በተለይ ዝውውር መብት የተሰጠው የደቡብ ክልል እግርኳስ ፌዴሬሽን የታገደውን የክለቡ የዝውውር መብት ካጸደቀ ሌላ ውዝግብ ከብሄራዊ ፌዴሬሽኑ እንዳይገጥመው ተሰግቷል።
አስተያየት ይስጡ