መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ “ጥሩ እግር ኳስን የሚጫወት ቡድን አለን፤ ደረጃችንም የሚሻሻል ነው “ቡልቻ ሹራ /ሰበታ ከተማ/
ሰበታ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

“ጥሩ እግር ኳስን የሚጫወት ቡድን አለን፤ ደረጃችንም የሚሻሻል ነው “ቡልቻ ሹራ /ሰበታ ከተማ/

አጋራ
አጋራ

“ጥሩ እግር ኳስን የሚጫወት ቡድን አለን፤ ደረጃችንም የሚሻሻል ነው “
“ተደጋጋሚ ጎሎችን ማስቆጠር ይጠበቅብኛል”

ቡልቻ ሹራ /ሰበታ ከተማ/

በሰበታ ከተማ ክለብ የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ ውስጥ ጥሩ እንቅስቃሴን ከሚያሳዩት ተጨዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ቡልቻ ሹራ ስለ ቡድናቸው እና ስለ ራሱ ለሀትሪክ ድረ-ገፅ አስተያየቱን ሰጥቷል፤ ተከታተሉት።

ስለ ሰበታ ከተማ የዘንድሮው የቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊግ ተሳትፎ
“የእዚህ ዓመት የውድድር ተሳትፎአችንን በተመለከተ በሜዳ ላይ ከሚታየው የጨዋታ እንቅስቃሴ አንፃር ቡድናችን ጥሩ ነው። እግር ኳስን አዝናኝ በሆነ መልኩ የሚጫወት ጥሩ ቡድንም አለን። በተለይ ደግሞ በባህር ዳር ላይ ያለን አቋም በሽንፈት ከመጣንበት ጅማ ከተማ አኳያ ሲታይም ቡድናችን ላይ ብዙ ለውጦችም አሉት። ከእነዚህም መካከል ሊጠቀሱ የሚችሉት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ተሰጥቶን በነበረው የእረፍት ወቅት ላይ ወደ ሰበታ ከተማ ተመልሰን መጥተን እና ጥሩም ተዘጋጅተን ነበርና የቀጣይ ጨዋታዎቻችን ላይ ተረጋግቶ ኳስን መጫወት መቻላችንና አሰልጣኛችን የሚነግረንንም ይኸውም ያለንን ነገር በሜዳ ላይ እንድንሰጥም ለማድረግ መቻላችን ጥሩነታችንን እያሳየን ይገኛል”።

በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ ከመሪው ቡድን ፋሲል ከነማ ጋር ነጥብ ተጋርተው ስለወጡበት የሰሞኑ ጨዋታ

“ፋሲል ከነማ የሊጉ ጠንካራ እና ትልቅ ቡድን ነው። ከእነሱም ጋር ተጫውተን ነው አቻ የተለያየነው። በዛ ጨዋታ በሜዳ ላይ እንቅስቃሴም ሆነ በስነ ልቦናው ጥሩ ነበርን። ከእነሱም በተሻለ እኛ በተለይም ደግሞ በሁለተኛው አጋማሽ ላይ ጥሩ ልንንቀሳቀስ ችለናል። በመጨረሻም የድል ውጤቱ ባይሳካም ነጥብ መጋራታችን በራሱ መጥፎ የሚባል ውጤት አይደለም”።

በሜዳ ላይ ጥሩ እግር ኳስን ትጫወታላችሁ እንደምትባሉት ሁሉ በውጤት ደረጃ አልታደላችሁም ስለመባሉ

“አዎን እውነት ነው በተለይ ጥሩ እግር ኳስን ከመጫወታችን ጋር በተያያዘ ይሄን ያልነው እኛ ብቻ ብንሆን ኖሮ ሌላ ስም ሊያሰጠን ይችል ነበር። ነገር ግን የስፖርት አፍቃሪው ጭምር ነው ስለ ቡድናችን ጥሩነት እየተናገረ ያለው። አሁን ላይ እኛ በምንፈልገው መልኩ ውጤትን ልናገኝ አለመቻላችን ሙሉ ቡድን እንዳንሆን አድርጎናል። የሚጎለን ነገርም አለ። ያ ስለሆነም አሁን ላይ ይሄን የያዝነውን አጨዋወት ከውጤት ጋር አብሮ ለማስኬድ ጥሩ ዝግጅትን እያደረግን ይገኛል። የቡድናችንን ድክመት ቀርፈንም ደረጃችንም ይሻሻላል”።

ለሰበታ ከተማ ጥሩ እንቅስቃሴ ብታደርግም ተደጋጋሚ ጎሎችን ለማስቆጠር አለመቻልህ

“ይሄን ችግሬን በጣም ላሻሽለው ነው የምፈልገው። ምክንያቱም ከፋሲል ከነማ ጋር በተደረገው ጨዋታ እኔ ግብ ሳስቆጥር ግቧን ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘኋት ነበረች። አሁን ላይ ጥሩ ልንቀሳቀስ ብችልም እንደጠበቅኩት ግን ግብ እያገባው አይደለምና ይሄ ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ ይሻሻላል”።

ስለ ቀጣይ ጨዋታዎቻቸው

“በቤት ኪንግ ፕሪምየር ሊጉ እየተጫወትን ያለነው በነጥብ ወደፊት ለመጠጋት እንጂ ለወራጅነት ስላልሆነ ከዚህ በኋላ ላሉን ግጥሚያዎች ለሁሉም ቡድኖች ነው እኩል ትኩረትን ሰጥተን ወደ ሜዳ የምንገባውና ለዛ በሁሉም መልኩ ዝግጁ ነን”።
ስለ አሰልጣኛቸው ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ
“ጥሩ ቡድን ሰርቷል። ነፃነትን ሰጥቶናል። ስንሳሳት ይረዳናል። ያለንን ችሎታም አውጥተን እንድንጫወትም እያደረገ ይገኛል። ቡድናችንን ቤተሰባዊ በሆነ መልኩም ሰርቶታልና እሱ ለየት ያለ እና ጥሩም አሰልጣኝ ሆኖብኛል”።

በመጨረሻ

“ሰበታ ከተማ በአብዛኛው በወጣት ተጨዋቾች ቢገነባም እኛን ሊጠቅሙ የሚችሉ ሲኒየር ተጨዋቾችንም አካቶ ይገኛል። እነሱ በብዙ መልኩ እየረዱን ይገኛል። የሁለታችን ቅንጅት እና የአሰልጣኛችን ታክቲክም ነው በእንቅስቃሴ ጥሩ እንድንሆን ያደረገን ከዚህ በኋላ ደግሞ ፈጣሪ በፈቀደ መልኩ ከፊታችን ያሉብንን ጨዋታዎች በማሸነፍ ያለንበትን ደረጃ ለማሻሻል እየተዘጋጀን ነው”።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...