በካፍ ኢንስትራክተርነቱ ሲያገለግል የነበረው ኢንስትራክተር አንተነህ እሸቴ ዛሬ ለሊት ማረፉ ተሰምቷል።
ኑሮውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ኢንስትራክተሩ በካፍ የሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ አሴሰር ሆኖ ሲሰራ ቆይቷል። የኢንስትራክተሮች ፓናል አባል የሆነው ኢንስትራክተሩ ከበርካታ ጊዜያት ህመም በኋላ ለሊቱን ማረፉን የቅርብ የሙያ ባልደረባው ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻው አስረድተዋል። ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጆች መጽናናትን እመኛለሁ።
አስተያየት ይስጡ