” ከጥሪው ሰአት ዘግይቶ የመጣ ዳኛ ያየሁት እናንተን ነው”
አቶ ኢሳያስ ጅራ/የፌዴ.ፕሬዝዳንት/
“ዳኞች ከ2አመት በፊት የሰጡት እድሜና ኢንተርናሽናል ለመሆን ያስመዘገቡት ዕድሜ መለያየቱ ተገቢ አይደለም”
አቶ መኮንን አስረስ/የዳኞች ኮሚቴ ም/ል ሰብሳቢ
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 250 ደረጃቸውን የጠበቁ ትጥቆችን ከአምብሮ በመግዛት ለዳኞች ሰጥቷል። ወደ 2 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ይኸው ትጥቅ ቱታ፣ ቅያሪ ቲሸርት፣ ማማቂያ፣ ፖሎ ቲሽርትና ቦርሳ መካተቱ ታውቋል። ከዚህ ውጪ የፌዴሬሽኑ ሎጎ ያለበት ኳስ ከአምብሮ ትጥቅ አምራች ኩባንያ መገዛቱን የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ አሳውቀዋል።
ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ጊዜ ስብሰባው ከተጠራበት ሰአት ዘግይቶ መጀመሩን በማስታወስ ዳኞቹ ዘግይተው መምጣታቸውን በመውቀስ “የዘገያችሁ ዳኞች እናንተ ናችሁ መደገም የለበትም” በማለት አሳስበዋል።
በዋቢ ሸበሌ እየተካሄደ ባለ መርሃግብር የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ም/ል ሰብሳቢ አቶ መኮንን አስረስ “ዳኞች ከ2 አመት በፊት የሰጡት ዕድሜና ኢንተርናሽናል ዳኛ ለመሆን ሲባል የተሰጠው ዕድሜ ፍጹም የተለያየ ነው”ሲሉ ተችተዋል።
አስተያየት ይስጡ