መነሻ ገጽ ሲዳማ ቡና “ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ የሲዳማ ህዝብ ነው፣ ሲሸነፍ ቡድኑ የመንግሥቱ ነው” አቶ መንግሥቱ ሳሳሞ /ተሰናባቹ የሲዳማ ቡና ፕሬዚዳንት/
ሲዳማ ቡናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

“ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ የሲዳማ ህዝብ ነው፣ ሲሸነፍ ቡድኑ የመንግሥቱ ነው” አቶ መንግሥቱ ሳሳሞ /ተሰናባቹ የሲዳማ ቡና ፕሬዚዳንት/

አጋራ
አጋራ

ሲዳማ ቡና እንደ አሁኑ ገንዘብ በደንብ በሚገኝበት ጊዜ አልነበረም የተመሰረተው… የክለቡና መስራች ይርጋለም ላይ ዱቄት ገዝተው እንጀራ በሽሮ በማዘጋጀት ቡድኑን ለ2 ወራት መግበው ክፍውን ጊዜ አልፈውታል፡፡ ቡድኑን እንደ ልጄ ነው የማየው ክፉና ደጉን አሳልፌበታለሁ የማይበርድ ፍቅር በውስጤ ያለው ለዚህ ነው ይላሉ ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት መንግሥቱ ሳሳሞ፡፡ 27 አመት በስፖርት አመራርነት፣ 14 አመት በሲዳማ ዞን ስፖርት ኮሚሽን ኃላፊነት፣ 14 አመት የሲዳማ እግር ኳስ መስራችና ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለው አላስፈላጊ ነው ያሉት ጫና ሲመጣ ቡድኑ ከተረፈና አሸናፊ የሚሆነው በኔ መልቀቅ ከሆነ በሚል ኃላፊነታቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለቀዋል፡፡

ባለት ዳርና የ4 ልጆች አባት የሆኑት አቶ መንግሥቱ ሳሳሞ ከሀትሪኩ ዮሴፍ ከፈለኝ ጋር በነበራቸው ቆይታ ስለ 14 አመት የአመራርነት ቆይታ፣ ስለ ሲዳማ ቡና ቀጣይ ጉዞ፣ ለምን ከኃላፊነት እንደለቀቁ፣ ስለ አዲሱ አሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌና ተሰናባቹ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ፣ ሜዳ ዘለው ስለሚገቡበትና ከዳኞች ጋር ለምን እንደሚጨቃጨቁና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሻቸውን ሰጥተዋል፡፡

ሀትሪክ፡- ከ14 አመት ቆይታ በኋላ ከሲዳማ ቡና ኃላፊነት ራስዎትን አግልለዋል… አዲስ ስሜት አልፈጠረብዎትም?

መንግሥቱ፡- ይሄን ክለብ የማየው እንደወለድኩት ልጄ አድርጌ ነው፤ ቤተሰቤን ሳልል ከክለቡ ጋር ስንከራተት ገንዘብ ስለምን ባለስልጣን ጋር ሄጄ ስማፀን እየኖርኩ ይህን ዘመን ሁሉ አሳልፌያለሁ፡፡ ቡድኑ በህይወት እንዲኖር እፈለጋለሁ… ምንም መጥፎ ነገር እንዲገጥመው አልሻም፡፡ አሁን የነበሩት አሰልጣኞች በተለይ ዘርአይ ሙሉ ከተጨዋችነት አንስቶ ቡድኑን አገልግሏል እነዚህ አመታቶች ለኔ ትልቅ ትርጉም ሰጥተውኝ አልፈዋል ከቡድኑ ስለይ ከአመራርነት ነው እንጂ ማገዝ ባለብኝ ሁሉ ከጎኑ ሆኜ እደግፋለሁ ቡድኑን እንዳልደግፍ የሚያደርገኝ ነገር የለም፡፡

ሀትሪክ፡- ከአመራርነትህ መነሳትዎ ያልዎትን ልምድ ክለቡ ማጣቱ በቀጣይ ጊዜ ላይ ክፍተት አይፈጥርም?

መንግሥቱ፡- ራሴን እንዳገልል ያደረገኝኮ ውጤት ጠፋ ተብሎ ጫና ሲመጣ የኔ መኖር ቡድኑን ከጎዳ ከእኔ በላይ ቡድኑ መኖር ስላለበት ነው… አሁን ቡድኑ አልወረደም 8ኛ ደረጃ ላይ ቢሆንም 45 ነጥቦች የሚገኝባቸው 15 ጨዋታዎች ገና ከፊታችን አሉ ቡድኑ ውስጥ ያለውን ክፍተት አይተን 2 አጥቂዎችን አካተን ከተጓዝን ስብስቡ አስተማማኝ ነው… አደጋ ውስጥ ገብቷል ብለን አናምንም ተጠናክረን ውጤት መቀልበስ አለብን ብለን እየሰራን እያለ ጫናው ሲበዛ ራሴን ማግለልን መርጫለሁ፡፡ ቡድኑ ውስጥ የተሻለ ሰው እንዲገባ እፈልጋለሁ እኔና የቡድኑ መሪዎች የምናስበው ተመሳሳይ ካልሆነ ብቆይም ምንም ለውጥ የለውም ተጨዋቾቹ ላይ ጣልቃ መግባት የጀመረ የውጪ ኃይል አለ እስካሁን ያልነበረው አሁን ልጆቹን የሚበጠብጥ ጣልቃ ገብቶ መከፋፈል የጀመረ ኃይል መኖሩን ሳውቅ ቅር ተሰኘሁ፡፡ እስካሁን ለውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት እጄን አልሰጠሁም አሁን ግን የአካባቢ ልጆች ናቸው አይደሉም፣ የውጪ ሀገር ዜጋ ነው አይደለም እያሉ የሚበጥብጡ ሲመጡ ሲከፋፈሉ ለቡድኑ ጠንቅ መሆናቸውን ሳይ በቃኝ ብያለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- አሁን ባለው የውስጥ ክፍፍል አሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌስ አይቸገርም?

መንግሥቱ፡- አሰልጣኝ ገ/መድህን ኃይሌ መታገዝ አለበት ብቻውን ምንም የሚያመጣው ነገር የለም ቦርዱና ስራ አስኪያጁ ለገ/መድህን ትከሻ ሆነው ከጎኑ ሊያግዙት ይገባል የቡድኑ ውጤት ለማሳመር ገ/መድህን ኃይሌን ማገዝ የሚፈልገውን ማድረግ የግድ ይላል አለበለዚያ ከባድ ይሆናል ገ/መድህን ኃይሌ ደግሞ ጣልቃ ተገብቶበት ይህን አድርግ እነ እንትናን አሰልፍ ተብሎ የሚሰራ አለመሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡

ሀትሪክ፡- ተሰናባቹ አሰልጣኝ ዘርአይ ሙሉ ስልኩን ዘግቧል መከፋቱን ሰምቻለሁ… የተሰናበተበት መንገድ ክብረ ነክ አይመስልም?

መንግሥቱ፡- አንድ አሰልጣኝ ለማሰናበት የቃል፣ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶ ነው ድንገት ተነስቶ ማሰናበት አይቻልም.. ይህ በደንብ ውስጥ አለ ሁለቱም አሰልጣኞች መብታቸው ተጠብቆ ነው መሰናበት የሚኖርባቸው… ውላቸውን ካልሰረዙ የገ/መድህን ኃይሌ አዲሱ ውል በፌዴሬሽን ሊፀድቅ አይችልም ፌዴሬሽኑም አይቀበልም በክብር በስምምነትና ውላቸውን ባከበረ መልኩ ነው መሰናበት ያለባቸው ቦርዱ አሰልጣኝ ዘርዓይን ትላንት በደብዳቤ ጠርቶታል /ቃለ ምልለሱን የሰራነው ትላንት አርብ ጠዋት ነው/

ሀትሪክ፡- ሲዳማ ቡና በቀጣይ ብሩህ ጊዜ ይገጥመዋል ብለው ያስባሉ?

መንግሥቱ፡- ቡድኑን ችግር የለበትም የህዝብ ድጋፍ ያለው ክለብ ነው አመራሩ ቀና ነው የተጠየቀውን ለማደረግ የተዘጋጀ አመራር ነው ለስሙና ለክብሩ የሚያገልግል ህዝብ ነውና መጪ ጊዜው ብሩህ ይመስለኛል ነገር ግን የውጪ ኃይል ፍላጎትን ማስቆም ያስፈልጋል የአሰልጣኙ ነፃነት መከበር አለበት የቡድኑ ነፃነትና ክብር ከተጠበቀ ሲዳማ ቡናን ውጤታማና ተፎካካሪ ቡድን ማድረግ ይቻላል መታወቅ ያለበት አሁንም ደግሜ መናገር የምፈልገው ገ/መድህን ኃይሌ ማንም ጣልቃ ገብቶ የሚያቦካበት አሰልጣኝ አይደለም… እውቀቱን በነፃነት እንዲያካፍል፣ በስርዓትና በሙሉ መብት ከተንቀሳቀሰ አሰልጣኙ ቡድኑን ወደ ውጤት ይመራል ብዬ አምናለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- በ14 አመት የአመራር ዘመንዎ የማይረሱት ነገር ምንድነው?

መንግሥቱ፡- ከከፍተኛ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ያደግነው እነ ደደቢት ቀርተው እኛ ዋንጫ ወስደን ነው በዚያ ጊዜ በርካታ ጫናዎች ነበሩብን ደስታና ስቃይ ተቀላቅሎ የገጠመኝ ያኔ ነው፡፡ አዲስ አበባ ድረስ ሸሽቼ ሞጆ ተደብቄ ወጥቼ ያደረኩበት ሊያጠፉኝ ከነበሩ ሰዎች የሸሸሁበትን ጊዜ አልረሳም፡፡ 2003 የፕሪሚየር ሊግ ክስተት ተብለን ከኢትዮጵያ ቡና፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት ጋር እስከ መጨረሻ ሰዓት ድረስ የተናነቅንበትን ጊዜ አልነበረም፤ በታዳጊ ፕሮጀክት ደግሞ እነ ሙሉጌታ ምህረት፣ አዳነ ግርማ፣ ሽመልስ በቀለ በሲዳማ ፕሮጀክቴ የተገኙ የመጀመሪያዎቹ ውጤቶቼ ናቸው፡፡ የሀዋሳ አርቴፊሻል ሜዳ ጫካ እያለ መንጥሬ ያሳጠርኩት እኔ ነኝ፡፡ ከዞኑ አስተዳደር 180 ሺ ብር ተቀብዬ ለአራት ኮትራክተር አከፋፍዬ እንዲሰራ አድርጌያለሁ፤ በሲዳማ ቡና በርካታ ገጠመኞችና ታሪኮች አሉኝ በእስካሁን ቆይታዬ ደስተኛ ነኝ፡፡

ሀትሪክ፡- መንግስቱ ሳሳሞ የቡድኑ ውጤት ሲጠፋ ወይም በርካታ ግብ ሲቆጠርበት፣ ዳኝነቱ ተበላሸ ብለው ካመኑ ዘለው ወደ ሜዳው ወርደው ቅሬታዎትን ያቀርባሉ ይከራከራሉ.. ምንድነው ምክንያቱ ለሲዳማ ቡና ያለዎት ፍቅር?

መንግሥቱ፡-/ሳቅ በሳቅ/ ወይ ፍቅር.. ፍቅር ብቻ አይደለም… ቡድኑ ሲያሸንፍ ህዝቡ የኔ ነው ብሎ አጨብጭቦ እልል እያለ ይቀበላል ሲሸነፍ መንግሥቱ ይሰድባል /ሳቅ/ ቡድኑ በህይወቴ ትልቅ ታሪክ አለው ለህዝቡ ነግሬያለሁ ሲዳማ ቡና ሲያሸንፍ የሲዳማ ህዝብ ነው ሲሸነፍ ቡድኑ የመንግሥቱ ነው /ሳቅ በሳቅ/ ይህ ሁሉ ጫና ያመጣው የስሜት ለውጥ ነው የሚታይብኝ… ይሄ አባባል በከተማው ውስጥም ሆነ በህዝቡ ዘንድ ይታወቃል፡፡

ሀትሪክ፡- እስኪ ስለቤተሰቦችዎ አውሩኝ… የአቶ መንግሥቱ ቤተሰብ ዙሪያ ብዙ የሚታወቅ ነገር የለም?

መንግስቱ፡- ባለቤቴ ወ/ሮ አማረች ፋንታ ትባላለች፡፡የ4 ልጆች አባት ነኝ ሁለቱ ልጆቼ ዘንድሮ ከዩኒቨርሲቲ ይመረቃሉ አንደኛው የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ ነው ሌላዋ ደግሞ ህፃናት ናት በጣም የምወደውና ለኔ ትልቅ ቦታ ያለው ቤተሰብ ነው ያለኝ፡፡ ለኑሮዬ ትልቅ ድጋፍ አድርገው ለዚህ አብቅተውኛል የነርሱ ሠላም ነው ያበረታታኝ ይህን ቤተሰቤን እንደምወዳቸውና እንደማከብራቸው መናገር እፈልጋለሁ፡፡

ሀትሪክ፡- ጨረስኩ… የሚያመሰግኑት ሰው አለ?

መንግሥቱ- በርካታ የሚመሰገኑ ሰዎችማ አሉ፤ ቡድኑ ተጠናክሮ እስኪመጣ ድረስ ከጎኔ የቆሙ ቤተሰቦቼን ማመስገን እፈልጋለሁ ቤተሰቤን ሳልል ውጪ እየጣልኩ እየሮጥኩ ቢሆንም ተረድተውና አግዘውኝ ደግፈውኝ አብረውኝ ስለኖሩ አመሰግናለሁ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ በዞኑ ካቤኔ ተመርጠው የመጡ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉንም አመራሮችና የቦርድ አባላት ከልብ አመሰግናለሁ፤ በጥላቻና በክፋት አይተውኝ አያውቁም በለመንኳቸው ጊዜ ያለውን ሰጥተው የጎደለውን ለመፈለግ የሚሄዱ ናቸው በሲዳማ ዞን አስተዳደር የነበሩ የካቢኔና የቦርድ አባላትን የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩትን በሙሉ ከጎኔ ሆነው ለረዱኝ አመሰግናለሁ… የሲዳማ ህዝብ ነፍሱ እስኪጠፋ ነው ቡድኑን የሚወደው እንደማንነት ጉዳይ አድርጎ ያየዋል ቀን ከለሊት ለሲዳማ ቡና ዋጋ የሚከፍል ህዝብ ነው እነርሱንም አመሰግናለሁ አርሶ አደሩ ለሲዳማ ቡና ወጪ ያደርጋል ምስጋናዬ ይደርሳቸው ማለት እፈጋለሁ በአጠቃላይ አብረውኝ ለነበሩ ሁሉ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...