መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ | በአሸናፊነት ጉዞ የቀጠለው ሀዲያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን አሸንፏል
ሀዲያ ሆሳዕናቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግአዳማ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | በአሸናፊነት ጉዞ የቀጠለው ሀዲያ ሆሳዕና አዳማ ከተማን አሸንፏል

አጋራ
አጋራ

 

ከምሳ ሰዓት በኋላ በተካሄደው መርሀ ግብር በአራተኛ ሳምንት አራፊ የነበሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች በአሸናፊነታቸው የቀጠሉበትን ውጤት ይዘው ለመውጣት ችለዋል ።

አዳማ ከተማዎች የመጀመሪያዎቹን ደቂቃዎች በግራ መስመር ከሚነሱ ኳሶች የማጥቃት አማራጮችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ሳይሳካላቸው ቀርቷል ።ሀድያ ሆሳዕናዎች በሌላ በኩል ተስፋዬ አለባቸው ከርቀት አክርሮ የአዳማው ግብ ጠባቂ ከያዘበት አስቆጪ ሙከራ በተጨማሪም ከሳጥን ውጪ በተሰራባቸው ጥፋት አምበሉ ዳዋ ሆቴሳ በግሩም ሁኔታ አክርሮ ወፈ ግብ ቢሞክርም በግብ ጠባቂው ሊድን ችሏል ።

 

አዳማ ከተማዎች አፈግፍገው በመጫወት በመልሶ ማጥቃት የሚገኙ እድሎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ሀድያ ሆሳዕናዎች በተቃራኒው ከመሀል ክፍሉ ተስፋዬ አለባቸው በረጅሙ ለፊት መስመር ተጫዋቾቹ በሚጥላቸው እንዲሁም በቀኝ መስመር ሱሌማን ሰሚድ በሚያሻግራቸው ኳሶች የግብ እድሎችን ለመፍጠር ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል ።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የጨዋታ እንቅስቃሴያቸው ፍሬ ያፈራላቸው ሀድያ ሆሳዕናዎች ሱሌማን ሰሚድ ከማዕዘን ምት ያሻማውን ኳስ አይሳክ ኢሴንዴ ከመረብ በማሳረፍ መሪ ሊያደርጋቸው ችሏል ።

 

በሁለቱም ቡድኖች መካከል የተቆራረጠ የኳስ ፍሰት ሲታይ ከግቡ መቆጠር በኋላ አስደንጋጭ ሙከራዎች ሳይታዩ የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ችሏል ።

በአዳማ ከተማ የማጥቃት እንቅስቃሴ የተጀመረው የሁለተኛው አጋማሽ የሀድያ ሆሳዕና ተከላካይ ክፍል መሳሳት ተከትሎ ታፈሰ ሰርካ ከርቀት ቢሞክርም የሀድያው ግብ ጠባቂ በቀላሉ ሊይዝበት ችሏል ። የታፈሰ ሰርካን ጥሩ የማጥቃት አቅም በሁለተኛው አጋማሽ ለመጠቀም ያሰቡት አዳማ ከተማዎች ተደጋጋሚ ጫናዎችን ለመፍጠር ሲሞክሩ ለግብ የቀረቡ የግብ እድሎችንም ሲፈጥሩ ታይተዋል ።

በማጥቃሩ ረገድ ተዳክመው የገቡት ሀድያ ሆሳዕናዎች ግብ ሱቆጠርባቸው ከቀኝ መስመር የተሻገረውን ሳጥን ውስጥ የተሞከረውን ኳስ ትግስቱ አበራ ከመረብ ላይ በማሳረፍ አቻ አድርጓቸው ቆይቷል ።

የማጥቃት ሚና ያላቸውን ተጫዋቾች ያስገቡት ሀድያ ሆሳዕናዎች በተለይም ከ ዱላ ሙላቱ ቅያሪ በኋላ ተጭነው ሲጫወቱ ሲታይ በእሱ ላይ በፍፁም ሳጥን ውስጥ የተሰራውን ጥፋት ዳዋ ሆቴሳ ሀድያ ሆሳዕናዎችን መሪ አድርጓቸዋል ። ከግቡ መቆጠር በኋላ ወደ ጨዋታው ለመመለስ አጥቂውን አብዲሳ ጀማል ቀይረው ቢገቡም ስኬታማ መሆን ያልቻሉት አዳማ ከተማዎች ተጨማሪ ግብ ለማስተናገድ ተገደዋል ።

ግብ ጠባቂው በረጅሙ ያሻማውን ኳስ ሳሊፎ ፎፎና የግል ብቃቱን በመጠቀም ሶስተኛውን ግብ ከመረብ በማሳረፍ የሀድያ አሸናፊነት ያረጋገጠች ግብ ከመረብ አሳርፏል ። ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳዕና በሊጉ አንድም ሽንፈትን ያልቀመሰ ቡድን ለመሆን ሲችሉ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጠዋል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...