መነሻ ገጽ ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ ኢንስትራክተር ሠዉነትቢሻው በተለይ ለ hatricksport.com ከጋቦን በቀጥታ
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ኢንስትራክተር ሠዉነትቢሻው በተለይ ለ hatricksport.com ከጋቦን በቀጥታ

አጋራ
አጋራ

በአዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ወደ ጋቦን ያመሩት ኢንስትራክተር ሠዉነት ቢሻው በጋቦን ቆይታቸውና በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን በተለይ ለ hatricksport.com ድህረ-ገፅ ገለፁ።

በጋቦን  ምድር እየተካሄደ የሚገኘውን 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአካል ተገኝተው እንዲከታተሉ በአዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ማኔጅመንት ውሳኔ ወደ ዉድድሩ ስፍራ ያመሩት ኢንስትራክተር  ሠዉነት ቢሻው “ከአዉሮፕላን ከወረድኩ ጀምሮ የተደረገልኝ አቀባበልና እዚሁ የሚገኙ የፍትቦል ሠዎች በደ/አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት ብ/ቡድናችን ባሳየው አቃም ደስተኛ  መሆናቸውን መግለፃቸው ያልጠበቁት ሆኖብኛል”ብለዋል ።”ጋቦን ኤርፖርት ስደርስ የተቀበለኝ ግብፅን ለሶስት  ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮና ያደረገው ሀሰን ሺአታ መሆኑ የተለየ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል” ያሉት ኢንስትራክተሩ “ደ/አፍሪካ ለነበረው ብ/ቡድንና ለእኔ ያላቸውን አድናቆት መግለፃቸው ፍፁም ያልጠበቁት ነዉ”ሲሉም ተናግረዋል ። ከእሳቸው ሌላም አንድ ኬንያዊ ጋዜጠኛ በተመሳሳይ”ደ/አፍሪካ ላይ ይዘኸው የቀረብከዉ ቡድን እንኳን በእናንተ በኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ፉትቦልም የማይዘነጋ ነዉ፤ለአንተም ለቡድንህም ትልቅ ክብር አለኝ” ብሎ ለማስታወሻ አብሮኝ ፎቶ ተነስቷል።በማለት የገለፁት ኢንስትራክተሩ የዛሬውን የግብፅና የቡርኪናፋሶ ጨዋታ ለመከታተል ሠዓቱን እየተጠባበቁ ሲሆን ቀደም ሲልም የቱኒዚያና የቡርኪናፋሶ ጨዋታን በአካል ተገኝተው መከታተላቸውንም ተናግረዋል።”ጋቦን ሁሉም ነገራ በጣም ዉድ ከተማ ከመሆንዋ ዉጪ በቆይታዬ ፍፁም ደስተኛ ነኝ” በማለት ለሀትሪክ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ከጋቦን በስልክ ገልፀዉለታል።

*ፎቶ – (ኢንስትራክተር ሠዉነት ቢሻው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ጋር)

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜና እረፍትዜናዎች

የጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ አጭር የህይወት ታሪክ

ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ከእናቱ ከወ/ሮ ጌጤ ገ/ስላሴ እና ከአባቱ ሀምሳ አለቃ ወልዴ...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣ

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...

ሀትሪክ ስፖርትጋዜጣዜናዎች

ሀትሪክ አሁንም ቀጠሮ ማክበር ስልጣኔ ነው በሚለው አቋሟ ጸንታለች

ቅዳሜ ጠዋት በቀጠሮ  ቀናችን  እርስዎ ጋዜጣዋን በእጅዎ ያስገቡ እንጂ አዳዲስና ያልተሰሙ መረጃዎችን...