በአዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ሙሉ ወጪያቸው ተሸፍኖ ወደ ጋቦን ያመሩት ኢንስትራክተር ሠዉነት ቢሻው በጋቦን ቆይታቸውና በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኛ መሆናቸውን በተለይ ለ hatricksport.com ድህረ-ገፅ ገለፁ።
በጋቦን ምድር እየተካሄደ የሚገኘውን 31ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በአካል ተገኝተው እንዲከታተሉ በአዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ ማኔጅመንት ውሳኔ ወደ ዉድድሩ ስፍራ ያመሩት ኢንስትራክተር ሠዉነት ቢሻው “ከአዉሮፕላን ከወረድኩ ጀምሮ የተደረገልኝ አቀባበልና እዚሁ የሚገኙ የፍትቦል ሠዎች በደ/አፍሪካው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት ብ/ቡድናችን ባሳየው አቃም ደስተኛ መሆናቸውን መግለፃቸው ያልጠበቁት ሆኖብኛል”ብለዋል ።”ጋቦን ኤርፖርት ስደርስ የተቀበለኝ ግብፅን ለሶስት ጊዜ የአፍሪካ ሻምፒዮና ያደረገው ሀሰን ሺአታ መሆኑ የተለየ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል” ያሉት ኢንስትራክተሩ “ደ/አፍሪካ ለነበረው ብ/ቡድንና ለእኔ ያላቸውን አድናቆት መግለፃቸው ፍፁም ያልጠበቁት ነዉ”ሲሉም ተናግረዋል ። ከእሳቸው ሌላም አንድ ኬንያዊ ጋዜጠኛ በተመሳሳይ”ደ/አፍሪካ ላይ ይዘኸው የቀረብከዉ ቡድን እንኳን በእናንተ በኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ፉትቦልም የማይዘነጋ ነዉ፤ለአንተም ለቡድንህም ትልቅ ክብር አለኝ” ብሎ ለማስታወሻ አብሮኝ ፎቶ ተነስቷል።በማለት የገለፁት ኢንስትራክተሩ የዛሬውን የግብፅና የቡርኪናፋሶ ጨዋታ ለመከታተል ሠዓቱን እየተጠባበቁ ሲሆን ቀደም ሲልም የቱኒዚያና የቡርኪናፋሶ ጨዋታን በአካል ተገኝተው መከታተላቸውንም ተናግረዋል።”ጋቦን ሁሉም ነገራ በጣም ዉድ ከተማ ከመሆንዋ ዉጪ በቆይታዬ ፍፁም ደስተኛ ነኝ” በማለት ለሀትሪክ ማኔጂንግ ኤዲተር ጋዜጠኛ ይስሐቅ በላይ ከጋቦን በስልክ ገልፀዉለታል።
*ፎቶ – (ኢንስትራክተር ሠዉነት ቢሻው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች ጋር)