“ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማን ወደ አዲስ አበባ ተመለስ ያለው አንድም የብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ አባል የለም”
…ከብሄራዊ ዳኞች. ኮሚቴ ውስጥ አዋቂ……“ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ ወደ አዲሰ አበባ የተመለሰው የኢንተርናሽናል ጨዋታ ጉዞ ስላለበት ነው”
ከቅርብ ምንጭ
ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው በቅጣት ሳይሆን ላለበት ኢንተርናሽናል ጨዋታ መሆኑ እየተነገረ ነው።
አርቢትሩ አዲስ አበባ ከተማና ፋሲል ከነማ ያደረጉትን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት የመራ ሲሆን በጨዋታው ለአዲስ አበባ ከተማ ያልተገባ የፍጹሞ ቅጣት ምት በመስጠቱና ግቡ በመቆጠሩ ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል። በጨዋታው የፈጠረውን ውጤት ለዋጭ ስህተት የተረዳው አርቢትሩ ለፋሲል ከነማ ተጨዋቾች ስህተት መስራቱን አምኖ አውቆ እንዳላደረገው በመግለጽ ይቅርታ በመጠየቅ ወደ አዲክ አበባ መመለሱ ታውቋል።
ብዙሃኑ የስፖርት ቤተሰብ አርቢትሩ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰው ብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ ተመለስ ብሎት ነው ቢሉም የጨዋታው ኮሚሽነር አዲሱ ነጋሽ ሪፖርት በጊዜው ባለመቅረቡ አንድም የኮሚቴ አባል ተመለስ እንዳላለውና የጨዋታውን ሂደት ለማየት ገና የኮሚሽነሩ ሪፖርት እየተጠበቀ መሆኑ ታውቋል።
ያም ሆኖ ኮሚሽነሩ አዲሱ ነጋሽ ዳኛው ውጤት ለዋጭ ስህተት መስራቱን የሚገልጽ ሪፖርት ለሊግ ኩባንያው የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ በማቅረባቸው ከቅጣት መትረፋቸው ታውቋል። እንደ መረጃዎች ኮሚሽነሩ ለሊግ ኩባንያው ያቀረቡት ሪፖርት አርቢትሩ ውጤት ለዋጭ ስህተት እንደሰሩ ቢገልጽም ለወራት የሚያስቀጣውን ከ7 ነጥብ በታች መስጠታቸውን የሚጠራጠሩ አልጠፉም።
የቅዲስ ጊዮርጊስና የመከላከያ ጨዋታ እንደተጠናቀቀ በፍጥነት ሪፖርታቸውን አቅርበው ውጤት ለዋጭ ስህተት ሰርተዋል የተባሉትን ኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤልን ፈጣን በሆነ መንገድ ያስቀጡት ኮሚሽነር አዲሱ ነጋሽ አሁን ድረስ የአዲስ አበባና የፋሲል ከነማን ጨዋታ ሪፖርት ለብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ አለማቅረባቸው ትዝብት ውስጥ ጥሏቸዋል።
ኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ላለበት የኢንተርናሽናል ጨዋታ ጉዞ ወደ አዲስ አበባ ከመመለሱ ውጪ ከዳኞች ኮሚቴ ደውሎ ተመለስ ያለው እንደሌለ ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል። ዛሬ በወጣ መረጃ ግን አርቢትሩ የደቡብ አፍሪካው ማማሎዲ ሰንዳውንስና የአንጎላው ፔትሮ አትሌቲኮ የሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ ለመምራት ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀና በመሆኑ ተመለስ ተብሎ ነው የሚለውን ግምት ፉርሽ አድርጎታል። በጉዳዩ ዙሪያ ምላሻቸውን ለማወቅ ወደ ኮሚሽነሩ አዲስ ነጋሽ ቢደወልም ስብሰባ ላይ ነኝ ከ30 ደቂቃ በኋላ ደውል በማለት ድጋሚ ከ45 ደቂቃ በኋላ ቢደወልላቸውም ይጠራ የነበረውን ስልካቸውን በመዝጋት ለስፖርት ቤተሰቡ ጥያቄ ምላሽ ሳይሰጡ ቀርተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከአዳማ ከተማ ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ሶስት ዳኞች በሌሎች መተካታቸው ተነገረ። ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ በኢንተርናሽናል አርቢትር በአምላክ ተሰማ፣ በኢንተርናሽናል አርቢትር ቴዎድሮስ ምትኩና በኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤል ምትክ ሌሎች ተተክተዋል። በዚህ መሰረት ኢንተርናሽናል
አርቢትር ዶክተር ሃ/የሱስ ባዘዘው፣ ፌዴ.አርቢትር ሀብታሙ መንግስቴና ፌዴራል ረዳት ዳኛ ክንፈ ይልማ በሶስቱ ዳኞች መተካታቸው ታውቋል።
አስተያየት ይስጡ