የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን የአቋም መግለጫ አወጣ !

 

እንደሚታወቀው የኢትዬጽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሰኔ 5 ባወጣው መግለጫ ላይ ክለቦች ከደሞዝ አከፋፈል ጋር በተያያዘ

* ለ ፕርሪሚየር ሊግ ክለቦች
* ለከፍተኛ ሊግ
* ለ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ
* ከ 20 አመት በታች ፕሪሚየር ሊግ እንዲህም በፌዴሬሽኑ ስር ተመዝግበው ለሚወዳደሩ ክለቦች በሙሉ ክለቦች በገቡት ውል መሰረት ለ ተጨዋቾች ደሞዝ እንዲከፍሉ እና ይህ ካልሆነ ግን እስከ ሐምሌ 5 ድረስ መክፈል ላልቻሉ ክለቦች ግልጋሎት እንደማይሰጥ መልእክቱን ማስተላለፉ አይዘነጋም ።

ይሁን እንጂ ማህበሩ በተደጋጋሚ ሲገልፀው እንደነበር ተጨዋቾቻችን ከደሞዝ አከፋፈል ጋር አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ሲገልፅ እንደነበር የሚታወስ ነው። ነገር ግን ጥቂት ክለቦች አሁንም መንግስት ያወጣውን አዋጅ በመተላለፍ እና ውል ባለማክበራቸው ምክንያት ተጨዋቾቻንን ለ ትልቅ የሞራል ኪሳራ እና የመብት ጥሰት ዳርጎዋቸዋል።

በመሆኑም ማህበራችን ከተቋቋመባቸው ዋነኛ አላማዋች አንደኛው የተጨዋቾች መብት ማስከበር ነው እና ከዚህ በኃላ ክፍያ ለማይፈፅሙ ክለቦች በህግ እንደምን ጠይቅ ከወዲሁ እናሳውቃለን ሲል በላከው ደብዳቤ አሳውቋል ።

via- EPFA

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor