ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ የቀድሞ አሰልጣኙን ለመቅጠር ከጫፍ ደርሷል

 

ከአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጋር ከቀናቶች በፊት የተለያዩት ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
የቀድሞ አሰልጣኛቸው ብርሀኔ ገብረእግዚአብሔርን ለመቅጠር ከጫፍ ደርሰዋል ::

የቀድሞ ኪራይ ቤቶች፣ ኢትዮጵያ መድህን፣አዳማ ከተማ እና መቐለ አሰጣኝ ብርሀነ ገብረእግዚአብሄር ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲን ከከፍተኛው ሊግ ወደ ፕሪምየር ሊግ ያሳደገ አሰልጣኝ ሲሆን። በ2010 የፕሪምየር ሊግ ወድድር ዘመን ወልዋሎን ጠንካራ ተፎካካሪ አድርገውት እንደነበሩ የሚታወስ ነው። በተለይም አሰልጣኙ የሚሰሯቸው ቡድኖች ኳስ ተቆጣጥሮ የሚጫወት ቡድን መሆናቸው እና የወልዋሎን አጨዋወት ባህል ጠንቅቅው የሚያውቁ ከሞሆናቸው የተነሳ አሰልጣኙን የወልዋሎ ቀዳሚ ተመራጭ እንዳደረጋቸው ተነግሯል። ፊርማቸውንም በጥቂት ቀናቶች ውስጥ አሳርፈው ምናልባትም በ 15ኛው ሳምንት ከአንድ አመታት በኋላ ወደ ሜዳው በመመለስ ወልቂጤ ከተማን የሚያስተናግደው ወልዋሎን እየመሩ ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። አሰልጣኙ የመውረድ ስጋት የተጋረጠበት ወልዋሎን የማዳን ሀላፊነት ተጥሎባቸዋል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor