መነሻ ገጽ ወልዋሎ ወልዋሎ አዲግራትና የቀድሞ አሰልጣኙ ተፋጠዋል
ወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ወልዋሎ አዲግራትና የቀድሞ አሰልጣኙ ተፋጠዋል

አጋራ
አጋራ


በዮሴፍ ከፈለኝ


በ2010 የተጀመረው የወልዋሎ አዲግራት
ዩኒቨርሲቲና የቀድሞ አሰልጣኙ ብርሃኔ ገ/
እግዚአብሔር ውዝግብ አሁንም አልተቋጨም፡
፡ የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊንና ይግባኝ ሰሚ
ኮሚቴዎች ክለቡ ለአሰልጣኙ ያልከፈለውን
የ6 ወር ደመወዝ እንዲከፍል ውሳኔ ቢሰጡም
ክለቡ ተግባራዊ ምላሽ አልሰጠም በሚል
ፌዴሬሽኑ ለክለቡ ምንም አይነት ግልጋሎት
እንደማይሰጥ በመግለፅ የመጨረሻ ያለውን
ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ይህን ተከትሎ ከሀትሪክ
ጥያቄ የቀረበላቸው የወልዋሎ አዲግራት
ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስና አስተዳደር ክፍል ኃላፊ
የሆኑት አቶ ኢድሪስ ከድር የፌዴሬሽኑ ውሳኔ
ተቃውመዋል፡፡ አቶ ኢድሪስ እንደተናገሩት
“የአሰልጣኙ ደመወዝን አንከፍልም ብለን
አልከለከ ልንም 3 ጊዜ ለፌዴሬሽኑ በላክነው
ደብዳቤ አሰልጣኙ አዲግራት የክለቡ ጽ/
ቤት ድረስ መጥተው ገንዘባቸውን መረከብ
እንደሚችሉ አስረድተናል እንቢ ብለው የቀሩት
እርሣቸው ናቸው፡፡ አዲግራት ይምጡና
ህጋዊ መንገድ ተከትለን የሚጠበቅባቸው
ግብር ከፍለው ለኦዲተር በሚመች መልኩ
ስራውን አጠናቀን ደመወዛቸውን ለመክፈል
ብንሞክርም አሰልጣኙ አልፈቀዱም ክለቡ
ታዲያ ምን ማድረግ ይችላል? ፌዴሬሽኑም
ይህን አካሄድ እያወቀ ቅጣቱን ማስተላለፉ
አሳዝኖናል” በማለት ተናገረዋል፡፡ አሰልጣኝ
ብርሃኔ ገ/እግዚብሔር ደግሞ ይህን የክለቡ
ምላሽ ውሸት ነው ሲሉ አስተባብለዋል፡
፡ አሰልጣኙ ለሀትሪክ ሲናገሩ “የክለቡ
ሰዎች የሚሉት በሙሉ ውሸት ነው 2 ጊዜ
አዲግራት ሄጄ ብሩን ሳይሰጡኝ ተመልሻለው
አንድ ጊዜ እንዲያውም የሚያስተናግደኝ ሰው
አጥቼ ተመልሻለው በሌለ ነገር ላይ ግብር
ክፈል ብለው ጊዜ እየወሰዱ ነው ደመወዜን
እንዲሰጡኝ ያላደረኩት ነገር የለም ፌዴሬሽኑስ
ቢሆን ይህን ሁሉ ሣያጣራ የዕገዳ ውሳኔ
የሚያስተላልፍ አይመስለኝም አሁንም የ6
ወር ደመወዜ እስኪፈለኝ ድረስ እታገላለሁ”ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ይሄ የፌዴሬሽኑ
እገዳ ደግሞ ወልዋሎ አዲግራትን 3ኛ ክለብ
ያደርገዋል፡፡ ከዚህ በፊት የሀገር ውስጥና
የውጪ ተጨዋቾች ደመወዝ ባለመክፈል
እገዳ የተጣለበት ጅማ አባጅፋር አሁንም
እገዳ ላይ ሲሆን ሶስተኛው ክለብ ድሬደዋ
ከተማ እገዳ ከተጣለብን ክለቡን እናፈርሳለን
በማለት አመራሮቹ ቢያስፈራሩም በህጋዊው
መንገድ የሚጠበቅባቸውን ደመወዝ በመክፈል
እገዳው ሊነሳላቸው ችሏል፡፡ በእገዳ ላይ
ያሉት የወልዋሎ አዲግራትና የጅማ አባጅፋር
ሁኔታ ለአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌና ለአሰልጣኝ
ጳውሎስ ጌታቸው የቅድመ ውድድር ዝግጅት
ጊዜ ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል ተብሎ
ተሰግቷል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...