መነሻ ገጽ ዜናዎች ጅማ አባጅፋር የበርካታ ተጨዋቾችን ዝውውር አጠናቀዋል
ዜናዎችየዝውውር ዜናዎችጅማ አባጅፋር

ጅማ አባጅፋር የበርካታ ተጨዋቾችን ዝውውር አጠናቀዋል

አጋራ
አጋራ

 

በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውር ዝምታን መርጠው የቆየቱ ጅማዎች በዚህ ሳምንት የ9 ተጨዋቾች ዝውውር አጠናቀዋል።

በርካታ የመሃል ሜዳ ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን ያጡት ጅማ አባጅፋር ኤልያስ አህመድ ከባህርዳር ከተማ፣ሃብታሙ ንጉሴ ከወልድያ፣አብርሃም ታምራት ከደደቢት በማስፈረም የመሃል ክፍላቸውን ለማጠናከር ሞክረዋል።

ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከባህርዳር ከተማ ጋር ጥሩ ጊዜ ያሳለፈው ኤልያስ አህመድ የቀድሞ አሰልጣኙን ነው ፓውሎስ ጌታቸው መንገድ በመከተል ጅማ አባጅፋር ማረፍያውን ሲያደርግ፣ደደቢት ላይ በቂ የመሰለፍ አድል ያላገኘው አብርሃም ታምራት እና አምና ከፍተኛ ሊጉ ላይ ከወልድያ ከተማ ጋር ቆይታ ያረገው ሃብታሙ ንጉሴን ማስፈረም ችለዋል።

በተጨማሪ አምና በመጀመርያ ዙር ደደቢትን በ2009 ወልዋሎን በአምበልነት መምራት የቻለው ተከላካዩ ኤፍሬም ጌታቸው ሌላኛው የፓውሎስ ጌታቸው ፈራሚ ነው።

ላይ ከተጠቀሱት ተጨዋቾች በተጨማሪ ሱራፋኤል አወል ከሰበታ ከተማ፣ከአዳማ ጋር በውዝግብ የተሞላ የውድድር አመት ያሳለፈው ብዙአየው አንደሻው፣አማኑኤል ጌታቸው ከጅማ አባቡና፣ሰዒድ ይመር ከአርባምንጭ ከተማ፣ተመስገን ደረሰ ከወልቂጤ ከተማ ማስፈረም ችለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ 70 እንደርታዜናዎች

ገረሱ ሸመና መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቀለ

በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል። በኢትዮጵያ እግር...

ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...