መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኝ ስቴዋርት ሃል ለቅዱስ ጊዮርጊስ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

አሰልጣኝ ስቴዋርት ሃል ለቅዱስ ጊዮርጊስ የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል፡፡

አጋራ
አጋራ

 

እንግሊዛዊው አሰልጣኝ ስቴዋርት ሃል ላለፉት ስምንት ወራት ፈረሰኞቹን ሲያሰለጥኑ የነበሩት ሲሆን በዛሬው እለት የመልቀቂያ ደብዳቤያቸውን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር አስገብተዋል ሲል ክለቡ በይፋዊ ገፁ (#Saint George S.A) አስታውቋል።
አሰልጣኙ በዛሬው እለት በልምምድ ሜዳ ያልተገኙ ሲሆን ከክለቡ ውጤት ማጣት ጋር ተያይዞ ስራቸውን በገዛ ፍቃዳቸው ለመልቀቅ ነው የስንብት ደብዳቤ ያስገቡት።
ይሁንና የአሰልጣኙን የስንብት ደብዳቤ በተመለከተ ከክለቡ የቦርድ አመራር ምላሽ እየተጠበቀ ነው።
በ2011 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የ24 ሳምንታት ጉዞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወጥ አቋም ባለማሳየት 39 ነጥቦችን ሰብስቦ በሊጉ የደረጃ ሰንጠራዡ አራተኛ ላይ ይገኛል፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ 14 ጊዜ ሲያነሳ ፤ ባለፈው ዓመት ዋንጫውን በጅማ አባ ጅፋር የተነጠቀ ሲሆን ዘንድሮም ሊጉ ሊጠናቀቅ የስድስት ጨዋታዎች ዕድሜ እየቀሩት ከመሪው መቐለ 70 እንደርታ በዘጠኝ ነጥብ እርቆ ይገኛል፡፡

አጋራ
ቀዳሚ ልጥፍ የእርስዎ ምርጫን ሀትሪክ ስፖርት ያንብቧት ሀትሪክ ስፖርት ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃ ተወዳጅ ጋዜጣዎ ስትሆን በእዚህ ሳምንት የማክሰኞ እትሟ የሚከተለውን ዘገባ ይዛ ወጥታለች፡፡ ሀትሪክን ማክሰኞ በገበያ ላይ ሲያገኟት ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ከምታስነብቦት የሀገር ውስጥ ዘገባዎቿ መካከል ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የጋዜጣው ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ለበርካታ ዓመታት ማለትም ለ50 ዓመታት ያህል በስፖርቱ ውስጥ ከመቆየት ባሻገር ብዙ ዋንጫዎችን በማንሳት የመጀመሪያ አሰልጣኝ የሆኑትን ውጤታማውን አሰልጣኝ አስራት ኃይሌን በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ አናግሯቸው ምላሽን ሰጥቷል፡፡ አሰልጣኝ አስራት ምን ብለው ይሆን፤ ሀትሪክ በፕሪምየር ሊግ ዙሪያም የፋሲል ከነማ ተጨዋቾች የሁኑትን አይናለም ዓይለ እና በዛብህ መለዮን እንዲሁም የሲዳማ ቡናውን ሀብታሙ ገዛኸኝን አናግራም እነሱም በቡድኖቻቸው ዙሪያ የሚሉት አላቸው፡፡

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...