በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታ ከሜዳው ውጪ 150ኪ.ሜ እርቆው እንዲጫወት ፌዴሬሽኑ ጅማ አባጅፋር ላይ ባስተላለፈው ቅጣት መሰራት በአዳማ አበበ በቂላ ስታዲየም ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ በአቻ ውጤት ጨዋታቸውን አጨናቀዋል፡፡
ጨወታው በጅማአባጅፋር አማካኝነት ሲጀመር የመጀመሪያ የጨዋታ አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች ኳስን አደራጅተው ወደ ጎል በመድረስ በጣም ጥሩ ነበሩ፡፡
በጨዋታው ከጅማ አባጅፋር በኩል የመሐል፡አማካዮቹ ኳስን በማቀጣጠል ፊት መስመር፡ላይ ለሚገኘው ጋናዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ እሚጡላቸው ኳሶች አደጋ ለመፍጠር ቅርብ ነበሩ፡፡ከሲዳማ ቡና በኩልም በተመሣሣይ በተደጋጋሚ ወደጎል በመድረስ ችለዋል፡፡ በተለይ ኦኪኪ አፎላቢ ያገኛቸውን የጎል አጋጣሚዎች ሳይጠቀምባቸው ቀርቷል፡፡ በተመሳሳይ የሲዳማ አማካይ ፍፁም ተፈሪ ጎል ለማግባት የቀረበችውን ኳስ ሳይጠቀምበት የቀረው አጋጣሚ እምታስቆጭ ነበረች፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሪያው አጋማሽ አኳያ በተቀዛቀዘ ሁኔታ የተጀመረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ሽኩቻና ንትርክ የበዛበት ነበር፡፡በ57ኛ ደቂቃ የሲዳማ ቡናው ግብጠባቂ መሣይ አያና በሰራው ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ሊሰናበት ችሏል፡፡ በረኛቸውን በቀይ ካርድ ለማጣት የተገደዱት ሲዳማዎች አብዱለጢፍ መሀመድን በተጠባባቂ ቦታ ላይ ያለውን ፍቅሩ ወዴሳን ቀይረው በማስገባት ቀሪዎቹን የጨዋታ ደቂቃዎች አፈግፍገው ለመጫወት ተገደዋል፡፡
በአንጻሩ ጅማ አባጅፋሮች ያላቸውን የተጫዋቾች ቁጥር ብልጫ ተጠቅመው በተደጋጋሚ ወደ ጎል በመድረስ ጎል ለማስቆጠር ያደረጉት ጥረት በአንድ አጋጣሚ የግቡ ብረት ሊመልስባቸው ችሏል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በእንዳለ ደባልቄ አማካኝነት ያደረጉት ጥረት ግብ ለማግኘት አልቻሉም፡፡ በዚሁ ጨዋታው ያለጎል 0-0 በሆነ ውጤት ሊጠናቀቅ ችሏል፡፡