በ18ኛው ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደደቢት በትግራይ ስታድየም ደቡብ ፖሊስን እስተናግዶ በመድሃንየ ብርሃኔ ብቸኛ ግብ አሸነፈ።መቐለ 70 እንደርታ ከገጠመው ቡድን ፋሱይኒ ኑሁን በመድሃንየ ታደሰ፣እብዱላዚዝ ዳውድን በእንቶንዮ እባውላ፣እሸናፊ እንዳለን በየአብስራ ተስፋዬ እንዲሁም እቤል እንዳለን በዳግማዊ እባይ ሲቀይሩ ደቡብ ፖሊስ በበኩላቸው እበባው ቡጣቆን በዘሪሁን እንሼቦ፣የተሻ ግዛውን በብርሃኑ በቀለ፣ኪዳኔ እሰፋን በብሩክ እየለ፣በሃይሉ ወገኔ በሄኖክ እየለ ቀይረው ጨዋታውን ጀምረዋል።
ደደቢቶች በሙከራ ደቡብ ፖሊስ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ወስደው በታዩበት የመጀመርያው እጋማሽ ጥሩ ፋክክር ታይቶበታል።ሰማያዊዎቹ ከዚህ በፊት ከሚጠቀሙት ኣጨዋወት በተለየ መልኩ ረጃጅም ኳሶችና ፈጣን መልሶ ማጥቃት ላይ ትኩረት በማድረግ የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል።ከሚታወቅበት የቀኝ ተከላካይ መስመር በተለየ መልኩ ፊት ቀኝ መስመር ላይ የተሰለፈው መድሃንየ ብርሃኔ እና ፊት እጥቂው ፊሱይኒ ኑሁ የነበራቸው ጥምረት የደቡብ ፖሊስ ተከላካይ ክፍል ሲረብሽ ነበር።ጨዋታው በተጀመረ በ5ኛው ደቂቃ መድሃንየ ብርሃኔ ከቀኝ መስመር ያሽልማውን ኳስ ፋሱይኒ ኑሁ በግምባሩ የገጨው ኳስ የግቡን ቀዋሚ ብረት ታኮ ወጥቷል።ከዚህ ሙከራ ሁለት ደቂቃ በኃላ በፍፁም ቅጣት ሳጥን ውስጥ ከቀኝ መስመር እለምእንተ ካሳ መሬት ለመሬት ያሻማው ኳስ ግብ ጠባቂው ሀብቴ ከድር ሲተጋው ከአጠገቡ የነበረው መድሃንየ ብርሃኔ እግኝቶት ደደቢቶችን መሪ ማድረግ ችሏል።ከግቡ መቆጠር በኃላ ካሱን ተቆጣጥረው የተጫወቱት ደቡብ ፖሊሶች ይህ ሚባል የጠራ የግብ እድል መፍጠር ባይችሉም በብሩክ እየለ እና በረከት ይስሃቅ እማካይነት ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል።ደደቢቶችም በፈጣን መልሶ ማጥቃት እድሎችን ሲፈጥሩ ነበር የዚህ ማሳያም መድሃንየ ከቀኝ መስመር እሻምቶት ፋሱይኒ በቀኝ እግሩ የመታው ጠንካራ ምት በተመሳሳይ በግራ መስመር እጥቂነት የተሰለፈው እንዳለ ከበደ ከርቀት የመታው ኳስ ተጠቃሽ ሙከራዎች ናቸው።
በሁለተኛው እጋማሽ የመጀመርያ 30 ደቂቃዎች ደደቢቶች ከመጀመርያው እጋማሽ በተሻለ መልኩ ኳሱን ተቆጣጥረው ለመጫወት ሞክረዋል።በተደጋጋሚ ፋሱይኒ ኑሁ ላይ በሚሰሩ ጥፋቶች ቅጣት ምቶችን ያገኙት ደደቢቶች 55ኛው ደቂቃ በግምት ከ30 ሜትር እካባቢ ያገኙትን ቅጣት ምት ፋሱይኒ በቀጥታ ቢመታውም ጨዋታው ላይ ጥሩ የነበረው ሀብቴ ከድር እድኖበታል።
- ማሰታውቂያ -
ቢጫ ለባሾቹ ወልዋሎዎች በኤፍሬም እሻሞ ና ተቀይሮ በገባው ሰመረ ካህሳይ አማካኝነት ሙከራዎቹን ቢያደርጉም እቻ ሚያደርጋቸውን ግብ ማግኘት ሳይችሉ ጨዋታው በኢትዮጵያ ቡና እሸናፊነት ተጠናቋል።
ድሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና ከእምስት ተከታታይ ሽንፈቶች በኃላ ወደ እሸናፊነት እንዲመለሱ አድርጓቸዋል።