በኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ተስተካካይ መርሃ ግብር ሽሬ ላይ ወልዋሎ አዲግራት ከ መቐለ ከተማ ሰኞ 9 ሰዓት ሊደረገ ኘሮግራም ወጦለት የነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከፀጥታ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የክልሉ ኮማንድ ፖስቱ በማገዱ ጨዋታው እንደማይካሄድ ሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ ከውስጥ ምንጮቿ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል።
በሊጉ 17ኛ ሳምንት ጨዋታ ወልዋሎ አዲግራት መቐለ ከተማን በአሳሪ አልማሀዲ የመጀመሪያ አጋማሽ በተቆጠረች ግብ እየመራ ጨዋታው በደጋፊዎቻቸው ረብሻ መቋረጡ እሚታወስ ነው። የሊጉ አስተዳዳሪ አካል የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጨዋታው እንዳማይካሄድ ከክልሉ የፀጥታ ሀይል ጨዋታውን ማገዱን አስመልክቶ ደብዳቤው እንዳልደረሰው ሀትሪክ ስፖርት ድህረገጽ አረጋግጣለች።