መነሻ ገጽ ሪፖርት ሪፖርት | የሊጉ መሪ ደደቢት በባለሜዳው ወላይታ ድቻ ሽንፈት አስተናግዷል
ሪፖርትወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግደደቢት

ሪፖርት | የሊጉ መሪ ደደቢት በባለሜዳው ወላይታ ድቻ ሽንፈት አስተናግዷል

አጋራ
አጋራ

በ16ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ ዛሬ በብቸኝነት በሶዶ ስታዲዬም ወላይታ ድቻ ከ ደደቢት ያደረጉት ጨዋታ በባለሜዳዎቹ 1ለምንም አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ፡የሊጉ መሪ ደደቢት ከተከታዬቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት የሚያሰፋበትን ዕድል አባክኗል፡፡

በበርካታ ደጋፊዎች ታጅቦ 9:00 ሲል በሶዶ ስታዲዬም በተካሄደው የወላይታ ድቻና የደደቢት ጨዋታ ባለሜዳዎቹ ድቻዎች ጨዋታው ከመጀመሩ አስቀድመው የደደቢቱ አጥቂ ጌታነህ ከበደ በፌደሬሽኑ ዲስፕሊን ኮሚቴ የተላለፈበትን የጨዋታ ቅጣት አልጨረሰም በሚል የክስ ቻርጅ ለአራተኛ ዳኛው አስይዘዋል፡፡

ባለሜዳዎቹ ድቻዎች በጨዋታው በአፍሪካ ኮንፌደሬሺን ካኘ ከሜዳቸው ውጭ ወደ ካይሮ አቅንተው የግብፁን ዛማሌክ ካሸነፉበት የመጀመሪያ ቋሚ 11 ተሰላፊዎች የ2 ተጨዋቾችን ለውጥ ሲያደርግ ዘላለም እና በዛብህን በማሳረፍ አምረላ እና ፀጋዬን ቀይረው አስገብተዋል፡፡

እንግዳው የሊጉ መሪ ደደቢት በ15ኛው ሳምንት ወደ ወልዲያ አቅንቶ በባለሜዳው ወልዲያ ከተማ 1ለምንም ፡ሽንፈትን ካስተናገዱበት የመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎች የ4 ተጨዋቾችን ቅያሪ በማድረግ ሲገቡ ታሪክን አስቀምጠው አማራን ሲያስገቡ በስዩም ቦታ ከድርን ሲያሰለፉ መሃል ክፍሉን ለማጠናከር ከቅጣት የተመለሰውን አስራትን በአቤል ቀይረው ሲያስገቡ በተመሳሳይ ከቅጣት የተመለሰውን ጨራሹን የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች ጌታነህን በአቤል ተክተው ወደ ሜዳ ገብተዋል፡፡

ዛሬ ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻና ደደቢት የተገናኙበት ጨዋታ ከጨዋታው አስቀድሞ በበርካታ የስፖርት ቤተሰብ ጨዋታው ትኩረትን ያገኘ ነበር፡፡በጥሩ መነቃቃት ላይ ያለው ወላይታ ድቻ ጨዋታውን በሜዳውና በደጋፊው ፊት እንደማድረጉ ዛማሌክን ባሸነፈበት ማግስት ቡድኑ ተጋጣሚውን ደደቢት እንደሚፈትነው የተጠበቀ ሲሆን በሌላ በኩል የሊጉ መሪ ደደቢት ከተከታዬቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት ጨዋታው ከሜዳው ውጭ ቢሆንም ሁለቱ ክለቦች ከፍተኛ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቅ ነበር ፡፡

ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች በታደመበት በሁለገቡ ሶዶ ስታዲዬም የተጀመረው ይሄው የቀኑ ብቸኛ የሊግ ጨዋታ ገና በጨዋታው መጀመሪያ ጀምሮ ከፍተኛ ፉክክርና ለተመልካች ማራኪ እንቅስቃሴ በተስተናገደበት የድቻና የደደቢት ጨዋታ ግብ የተቆረው ገና በጨዋታው መጀመሪያ ደቂቃ ነበር፡፡ባለሜዳዎቹ የጦና ንቦች በ3ኛው ደቂቃ ላይ ከመሃል ሜዳ ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል የተሻገረውን ኳስ አምረላ ደልታታ በጭንቅላቱ ኳስን ከመረብ ጋር በማገናኘት ክለቡን መሪ ማድረግ ችሏል፡፡

ሁለቱም ቡድኖች በሁለቱም የጨዋታ ክፍሌ ጊዜ ኳስን መስርተው ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል ለመግባት የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ተመልካቹን ቁጭ ብድግ የሚያስብል ነበር፡፡ሁለቱም ቡድኖች ከመከላከል ወደ ማጥቃት በሚያደርጉት ሽግግር ተመጣጣኝ ቢሆንም ባለሜዳዎቹ የተሻሉ ሲሆኑ ባለሜዳዎቹ የመሃል ሜዳ ክፍል በመቆጣጠርና ቶሎ ቶሎ ወደ ተቃራኒው ቡድን ክልል በመድረስም የተሻሉ ሁነው አምሽተዋል፡፡

በአንጻሩ እንግዳዎቹ ደደቢቶች በመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ ባለሜዳዎቹን ንቦች ላይ ጫና በመፍጠር ግብ ለማስቆጠር ቢጫዎቱም እንዳለመታደል ሁኖ የድቻን መረብ ላይ ኳስን ማሳረፍ ሳይችሉ ባመሹበት ጨዋታ ጌታነህ ከበደ ጎልቶ አምሽቷል፡፡ደደቢት ዛሬ ከሜዳው ውጭ መሪነቱን የሚያጠናክርበትን ዕድል ቢያመክንም በ29 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ ሲቀመጥ ፡ባለሜዳው ወላይታ ድቻ በማሸነፉ ነጥቡን 22 በማድረስ በሊጉ መሪ ደደቢት በ7 ነጥቦች ተበልጦ ደረጃውን ከ9ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል፡፡

የአሰልጣኞች አስተያየት

☞ዘነበ ፍስሃ -የወላይታ ድቻ አሰልጣኝ

በዛሬው ጨዋታ ቡድኔ ያሰብኩትን ያህል ባይጫወትም ተጋጣሚያችን ላይ ጫና ለመፍጠር ሞክረናል፡፡ ዕቅዳችን የነበረው ጨዋታውን ማሸነፍ ነበር ይህንንም አሳክተናል፡፡ ማሸነፍ በመቻላችንም ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡

☞ጌቱ ተሾመ -የደደቢት ምክትል አሰልጣኝ

ለጨዋታው በቂ የሚባል ዝግጅት ብናደርግም ገና በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ጎል ማስተናገዳችንና አጋጣሚዎችን መጠቀም ባለመቻላችን ዋጋ አስከፍሎናል ብለዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...