በ38ኛው የሸገር ደርቢ ፈረሰኞቹ ኢትዮጵያ ቡናን ሙሏለም መስፍን በጨዋታው መገባደጃ ደቂቃ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ 1-0 በመርታት የዋንጫውን የጉዞ ምዕራፍ ከአፍሪካ መድረክ መልስ ቀይሰዋል፡፡
ሳምንቱን ብዙ ሲባልለት የቆየው የመዲናዋ ትልቁ ደርቢ በበርካታ ብርቱካናማዎቹና ቡናማዎቹ ደጋፊዎች ህበረ ቀለምና ህብረ ዝማሬ ደምቆ ሜዳ ላይ ያንይህል ለተመልካች ማራኪ ሳይሆን ማምሻውን ፍፃሜውን አግኝቷል፡፡በጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊሶች ባለፈው ሳምንት በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጎንጎ ላይ በካራ ብራዛቢል በመለያ ምት ተሸንፈው ከውድድሩ ሲወጡ የተጠቀሙባቸውን የመጀመሪያ 11 ተሰላፊዎች በዚህ ጨዋታ የተጨዋች ለውጥ ሳያደርጉ ሲገቡ፡ በኢትዮጵያ ቡናዎች በኩል በ20ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዮር ሊግ በሜዳቸው ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2-1 ከረቱበት የመጀመሪያ ተሰላፊዎች የ3 ተጨዋቾችን ለውጥ ሲያደርጉ በሀይሌ ገ/ተንሳይ፡ወንድፍራው ጌታሁንና ኤሊያስ ማሞ ምትክ ትግስቱ አበራ፡መሱድ ሙሀመድና ካፕቲስቴ ሳነሚን ቀይረው ገብተዋል፡፡

ኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ በመሃል ዳኝነት በመሩት የሸገር ደርቢ ጨዋታ ቅዱስ ጊዬርጊሶች በ4-3-3 ፎርሜሽን ሲገቡ ኢትዬጵያ ቡናዎች በተመሳሳይ አሰላለፍ ጨዋታውን ጀምረዋል፡፡ጨዋታው በመሃል ሜዳ እንቅስቃሴ ላይ አዘንብሎ ሁለቱም ቡድኖች ጥንቃቄ ላይ አይመዝነው ሲጫዎቱ ባመሹበት ምሽት ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ለመመልከት 17 ያህል ደቂቃዎችን መጠበቅ የግድ ነበር፡፡በዚሁ ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናዎች ረጃጅም ኳሶችን ወደ ፊት በመጣል የግብ ዕድል ለመፍጠር ባደረጉት ጥረት ፈረሰኞቹ በሰሩት ጥፋት የተገኘውን ቅጣት ምት ቡናዎች ወደ ግብ ያሻገሩትን ኳስ የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኦዶንካራ ወደ ውጭ አውጥቶት ቡናዎች ያገኙትን የማዕዘን ኳስ ሳየይጠቀሙበት ባክኗል፡፡ኢትዬጵያ ቡናዎች በተደጋጋሚ ወደ ተጋጣሚያቸው የግብ ክልል በመድረስ ጫና ፈጥረው ለመጫዎት ቢሞክሩም በመልሶ ማጥቃት ሽግግር ላይ በተደጋጋሚ በሚሰሩ ጥፋተቶች ፈረሰኞቹ በ23ኛው ደቂቃ በሃይሉ አሰፋ በቅጣት ምት ወደ ግብ ያሻገረው ኳስ በቡና ተከላካዮች ተጨርፎ ወደ ውጪ በመውጣቱ ሌላ የማዕዘን ምት ቢያገኙም በተከላካዮች በቀላሉ ተመልሷል።

ጨዋታው በተደጋጋሚ በሁለቱም ቡድኖች በኩል በሚሰሩ ጥፋቶች በዳኛ ፊሽካ በመቆራረጥ ሲቀጥል በኢትዮጵያ ቡና በኩል አሁንም ረጃጅም ኳሶችን ተጠቅመው ግብ ለማግኘት ሲሞክሩ በቅዱስ ጊዮርጊስ በኩል ኳስን ከግብ ክልላቸው ጀምረው በመመስረት ለመጫወት ቢሞክሩም በኢትዮጵያ ቡና አማካኞች እየተቋረጠ ጨዋታው ቀጥሏል፡፡ከበርካታ ደቂቃዎች በሇላ ቡናዎች በ40ኛው ደቂቃ ሳሙኤል ሳኖሚ ባፕቲስት ፋዬ አመቻችቶ ያቀበለውን ኳስ ወደ ግብ ሞክሮት በጥሩ አቋቋም ላይ የነበረው ሮበርት ኦዶንኮራ ኳሱን በቀላሉ ተቆጣጥሮታል፡፡ሁኖም በድጋሚ በ43ኛው ደቂቃ ቡናዎች ያገኙትን የቅጣት ምት ሳኖሚ ሳይጠቀምበት የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ግብ ተጠናቆ ለእረፍት ወጥተዋል፡፡
በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ የተሻለ የኳስ ፍሰት ለመመልከት በተመልካቹ ቢጠበቅም እንደመጀመሪያው አጋማሽ ጨዋታው በሚሰሩ ጥፋቶች ሲታጀብ በ47ኛው ደቂቃ ፈረሰኞቹ በአሜ መሃመድ አስደናቂ የግል ብቃት ተከላካዮችን አልፎ የቡና የግብ ክልል ውስጥ ገብቶ የመታው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጭ ወጣ እንጅ መሪ መሆን ይችሉ ነበር፡፡ቡናዎች በበኩላቸው በ50ኛው ደቂቃ ከፈረሰኞቹ የግብ ክልል ጠርዝ ላይ ያገኙትን ኳስ ወደ ክብ ሞክረውት በሮበርት ድንቅ ብቃሲመክን አጠፋውን ለመመለስ ፈረሰኞቹ ባደረጉት ጥረት በ53ኛው ደቂቃ ኒኪማ ከመስመር ለአቡበከር ሳኒ ያሻገረችለትን አቡበከር በአግባቡ ሳይጠቀምበት በተከላካይ መነጠቁ የሚያስቆጭ ነበር፡፡በ56ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡናዎች በመልሶ ማጥቃት ይዘው የገቡትን ግልፅ ኳስ ሳይጠቀሙበት ሲባክን በ57ኛው ደቂቃ በመልሶ ማጥቃት የተመለሰውን ኳስ ፈረሰኞቹ አግኝተውት ወደ ግብ ክልል ሲያመሩ ሀሪሰን ከግብ ክልሉ ወጥቶ ኳሱን በቀላሉ ሲመልሰው በረጅሙ ወደ ግብ ባይሞክሩትም በተከላከዮች ተመልሷል፡፡

በ63ኛው ደቂቃ ፈረሰኞቹ በአዲስ ጉልበት የፊት መስመሩን ለማጠናከር ጋዲሳ መብራቴ በማስወጣት አዳነ ግርማን ወደ ሜዳ ባስገቡበት የጨዋታ እንቅስቃሴ በ66ደቂቃ ፈረሰኞቹ ግልፅ የግብ ዕድልን ፈጥረው በሃይሉ አሰፋ የመታው ኳስ በተከላካዮች ተመልሶ የመዓዘን ምት ሆኗል ሳይጠቀሙበት ሲባክን በ78ኛው ደቂቃ አዳነ ግርማ ከመስመር የተሻገረለትን ጥሩ ኳስ ወደ ግብኘት ቀየረው ሲባል ሳይጠቀመበት ሲባክን በ88ኛው ደቂቃ አበባው ቡጣቆ ከማዕዘን ምት ያሻገረውን ኳስ ሙሉዓለም መስፍን በግንባር በመግጨት የጨዋታውን ወርቃማ ጎል አስቆጥሮ ቡድኑን ቀዳሚ ሲያደርግ ኢትዮጵያ ቡናዎች በጨማሪው በ93ኛው ደቂቃ ጥሩ የጎል ዕድል አግኝተው አቻ መሆን የሚችሉበትን ዕድል ሳይጠቀሙት ጨዋታው በቅዱስ ጊዬርጊስ 1-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የጨዋታውን ውጤት ተከትሎ ፈረሰኞቹ 2 ቀሪ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀራቸው ነጥባቸውን 33 በማድረስ በደደቢት በግብ ክፍያ ተበልጠው ወደ 3ኛ ደረጃ ከፍ ሲሉ ኢትዬጵያ ቡናዎች በደረጃ ሰንጠረዡ ወደ 2ኛነት ከፍ የሚሉበትን ዕድል አባክነው በ32 ነጥብ ወደ 5ኛ ደረጃ ዝቅ ብለው ተቀምጠዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
☞አሰልጣኝ ቫስ ፒንቶ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
በመጀመርያው የጨዋታ አጋማሽ ኳስን ተቆጣጥረን የመጫወቻ ቦተታዎችን ክፍተት በመጠኑም ቢሆን ሰጥተናቸው የነበረ ቢሆንም በሁለተኛው አጋማሽ የነበረብኑን ክፍተቶቸች በማረም ጨዋታውን ተቆጣጥረን አሸንፈናል፡፡ይህን ጨዋታ ማሸነፋችን ለኛም ሆነ ለደጋፊዎቻችን ትልቅ ደስታን ፈጥሮልናል፡፡
☞አሰልጣኝ ዲዲዬ ጎሜስ – ኢትዮጵያ ቡና
በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ የተሻልን ነበርን ግብ አላስቆጠርንም እነሱ ግን በተሻሉበት የሁለተኛው አጋማሽ ግብ አስቆጠሩ፡፡በጨዋታው የተሻለ ስብስብ የነበረውን ተጋጣሚያችን በጨዋታ በልጠን ብንጫዎትም ውጤቱ ግን በአሳዛኝ ሁኔታ ተሸንፈናል፡፡
አስተያየት ይስጡ