መነሻ ገጽ ዜናዎች 🇪🇹የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ዩጋንዳ አቅንቷል።
ዜናዎች

🇪🇹የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ወደ ዩጋንዳ አቅንቷል።

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለመካፈል የመጀመሪያ የማጣርያ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ ከዩጋንዳ አቻቸው ጋር በሉጎጎስታር ታይምስ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል ፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ዩጋንዳ ከገባ በኋላ ከጋዜጠኞች ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ምክትል ዋና ፀሀፊ አቶ ሰለሞን ከጋዜጠኞች ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ወደ እናንተ አድርሰናል።

አቶ ሰለሞን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ “እዚህ ዩጋንዳ ለከ17 አመት በታች የሴቶች አለም ዋንጫ ማጣሪያ ነው የደረስነው፤ ለጨዋታው ዝግጁ ነን።” ብለዋል አቶ ሰለሞን አክለውም “ለዚህ ጨዋታ ቡድናችን በሆቴል ተሰባስቦ ለ11 ቀናት ልምምድ ሲሰራ ነበር፤ ለጨዋታው በአካል ብቃትም ሆነ በስነልቦና ረገድ በጥሩ ሁኔታ ተዘጋጅተናል።” ሲሉ ተናግረዋል።

ለጨዋታው 25 አባላት ያለው ልዑክ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀና ሲሆን ጨዋታው ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ሲል የሚጀምር ይሆናል።

ሀትሪክ ስፖርት ድረ ገጽም ለሴት ብሔራዊ ቡድናችን መልካም እድል እንዲገጥመው ትመኛለች!

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
መቐለ 70 እንደርታዜናዎች

ገረሱ ሸመና መቐለ 70 እንደርታን ተቀላቀለ

በሊጉ ለመቆየት እየዳዱ የሚገኙት መቐለ 70 እንደርታዎች ረዳት አሰልጣኝ ሾመዋል። በኢትዮጵያ እግር...

ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

“የቀዶ ጥገና ህክምና ይደረግለታል” የወላይታ ድቻ ስራ አስኪያጅ አቶ ምትኩ ሐይሌ

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ከባድ ጉዳትን ያስተናገደው ወጣቱ ተጫዋች ቅዱስ ቂርቆስ በምን...

ኢትዮጵያን በውጪዜናዎች

በካናዳ የኢትዮጵያዊያን የባህል እና ስፖርት ሊግ በይፋ ተመሠረተ

በካናዳ የኢትዮጵያ የባህል እና ስፖርት በሚል ስያሜ ሊግ ተቋቋመ። የኢትዮጵያን ባህል ለአለም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...