መነሻ ገጽ Uncategorized ፌዴሬሽኑ ከመመሪያ ውጪ የተጫዋቾችን ውል የሚያፈራርሙ ክለቦችን አስጠነቀቀ
Uncategorizedዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

ፌዴሬሽኑ ከመመሪያ ውጪ የተጫዋቾችን ውል የሚያፈራርሙ ክለቦችን አስጠነቀቀ

አጋራ
አጋራ

 

በኘሪሚየር ሊጉ ለሚጫወት ማንኛውም ተጨዋች ከነሐሴ 3 ቀን 2ዐ11 ዓ.ም ጀምሮ የደመወዙ ጣሪያ ታክስን ጨምሮ ብር 5ዐ,ዐዐዐ.ዐዐ (ሃምሳ ሺህ ብር) እንዲሆን 15 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ቢሾፍቱ ላይ መወሰናቸው ይታወቃል፡፡ፌዴሬሽኑ ውሳኔውን እንዲያስፈጽም ክለቦች በወሰኑት መሰረት ፌደሬሽኑ በቁጥር 2/ኢ.እ.ፌ አ-4/1069 ነሐሴ 08/12/2011 ዓ.ም በጻፈው የሰርኩላር ደብዳቤ ክለቦች በዚህ ውሳኔ መሰረት የተጫወቾችን ውል እንዲፈጽሙ መግለጹ ይታወቃል፡፡

ሆኖም ግን የተወሰነውን ውሳኔ በአግባቡ ከመፈፀም ይልቅ የተወሰኑ ክለቦች በተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ውል እየተዋዋሉ እና እያፀደቁ በተቃራኒው ግብር የማይከፈልበት ገንዘብ በህገ-ወጥ መንገድ ለተጫዋቾች ክፍያ እየፈጸሙ እንደሆነ ከተለያዩ ጠቋሚ የመረጃ ምንጮች ጥቆማዎች ደርሰውናል፡፡

በመሆኑም ፌደረሽኑ ይህንን ህገ-ወጥ ድርጊት ከተጫዋቾች ጋር በመመሳጠር በታክስ ስወራና ህገ-ወጥ በሆነ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ ካላችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን፤ መንግስት በራሱ የሚወስደው እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ፌደሬሽኑም በዚህ ህገ-ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርቶ በተገኘ ክለብ፤ የክለብ አመራርና ተጫዋቾች ላይ ከስፖርቱ ዓለም እስከ ማገድ የሚደርስ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ዛሬ ለክለቦች በላከው ደብዳቤ አሳውቋል ፡፡

ምንጭ ኢእፌ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

Uncategorized

FIFA temporarily lifts transfer ban on St. George

Saint George's has had its transfer ban imposed by FIFA temporarily lifted...

ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንፊፋ

ፊፋ ቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ጥሎት የነበረውን የዝውውር ዕገዳ በጊዜያዊነት አነሳ

ቅዱስ ጊዮርጊስ በአራት የቀድሞ ተጫዋቾች ቀርቦበት በነበረው ክስ በፊፋ ጥሎበት የነበረው የተጫዋቾች...