መነሻ ገጽ ዜናዎች ፌዴሬሽኑ ለማህበራት የሰጠው ቢሮ ከምስጋና ይልቅ ቅሬታ እንዲቀርብበት እያደረገው ነው
ዜናዎች

ፌዴሬሽኑ ለማህበራት የሰጠው ቢሮ ከምስጋና ይልቅ ቅሬታ እንዲቀርብበት እያደረገው ነው

አጋራ
አጋራ

በይስሕቅ በላይ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
የእግር ኳሱ ዋነኛ ባለ ድርሻ
አካላት ናቸው ላላቸው ማህበራት
ስራቸውን በሰከነና በተደራጀ መንገድ እንዲሰሩ
በማሰብ የሰጠው ቢሮ ከምስጋና ይልቅ ቅሬታ
አስነስቶበታል፡፡
ፌዴሬሽኑ ለአልጣኞች ማህበር፣ለዳኞች
ማህበርና ለተጫዋቾች ማህበር ለዕለት
ተዕለት ስራ ማከናወኛ የሚውል የመገልገያ
ቢሮ ቢሰጥም አንዳንድ ማህበራት የተሰጠን
ቢሮ የማህበራትን ክብርና ደረጃ የሚመጥን
አይደለም በማለት ቅሬታ እያሰሙ ነው፡፡
በዚህ በኩል በተለይ የአሰልጣኞች
ማህበር ፌዴሬሽኑ ለማህበሩ ቢሮ በመስጠት
ለመተባር መሞከሩን አመሰግነው ቢሮው
ግን ማህበሩንና በሀገሪቱ እግር ኳስ
ላይ ጉልህ አሻራ ያላቸውን የስመ-ጥር
አሰልጣኞች ክብርን የሚመጥን አይደለም
በማለት የተሰጣቸውን ቢሮ አጣጥለውታል፡
፡ “ቢሮ ለመስጠት የተወሰደው ተነሳሽነት
ላይ ቅሬታ የለንም ነገር ግን የተሰጠን ቢሮ
“ቢሮ ሰጠናቸው” ለማለት ካልሆነ በስተቀር
ክብራችንን የሚመጥን፤በእግር ኳሱ እድገት
ላይ የተሻለ ነገርን ለመስራት ምቹ የስራ
ድባብን የሚፈጥር አይደለም” ብለዋል፡፡
“ቢሮአችንን ለማደራጀት
ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች፣ግለሰቦችና
ድርጅቶች እናግዛችኋለን ብለው ቃል
ቢገቡልንም፤ለማህበራችን አባሎች ዋይፋይ
አስገብተን የኢንተርኔት አገልግሎት
በማግኘት በሙያቸው ዙርያ ጥናትና ምርምር
የሚያደርጉበትን መድረክ የመፍጠር ትልቅ
ህልም ቢኖረንም የተሰጠንን ቢሮ ይሄን
ለማድረግና ምቹ የስራ ድባብን የሚፈጥር
አይደለም” ብለዋል፡፡ “የስጦታ ትንሽ
ባይኖረውም አሁን በተሰጠን ቢሮ የቱ ጋር
ተቀምጠን…የቱ ጋር ተገናኝተን፣በምን ሁኔታ
ላይ ተወያይተን ነው በእግር ኳሱ ልማት ላይ
የምንሰራው?” በማለት የሚጠይቀው ማህበሩ
“የሆነ ጉሩኖ ውስጥ ከተቱን እንጂ ቢሮ ነው
የሰጡን ለማየት ይቸግረናል” በማለት በቅሬታ
የታጀበ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...