ፋሲል ከነማ የተጫዋቾችን ውል ማራዘሙን ቀጥሏል !

የዘንድሮው ዓመት የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ባለቤት ፋሲል ከነማ በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ከሚገኙ ክለቦች ውስጥ ዋነኛው ሲሆን የሁለት ተጫዋቾችን ውል ሲያራዝም ሁለት ተጨማሪ አዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረማቸው ተሰምቷል ።

በዘንድሮው የውድድር ዓመት ድንቅ እንቅስቃሴን በጋራ ማሳየት የቻሉት በዛብህ መለዮ እና ሽመክት ጉግስ በይፋ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት በአጼዎቹ ቤት የሚያቆያቸውን ውል ማራዘማቸው ይፋ ተደርጓል ።

በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም ከአሰልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር በመከላከያ ቤት መስራት የቻሉት ግብ ጠባቂው ይድነቃቸው ኪዳኔ እና የአማካይ ተጫዋቹ ፍቃዱ ዓለሙ ፋሲልን ከነማን የተቀላቀሉ አዲስ ተጫዋች ለመሆን ችለዋል ::

ፋሲል ከነማ በእስከ አሁኑ የዝውውር ሂደት የሰባት ተጫዋቾቹን ውል ሲያራዝም ሶሰት አዳዲስ ተጫዋቾች ቡድኑን ሊቀላቀሉ ችለዋል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor