ፋሲል ከነማ የተጫዋቹን ውል አራዘመ !

 

በዝውውር መስኮቱ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙት የዘንድሮው ዓመት የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ክብር ባለቤት ፋሲል ከነማ የሀብታሙ ተከሰትን ውል ማራዘማቸው ሀትሪክ ስፖርት ለማወቅ ችላለች ።

በአጼዎቹ ቤት በዘንድሮው የውድድር ዓመት በመሀል ሜዳ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴን በማሳየት የውድድር ዓመቱን ያሳለፈው ሀብታሙ በአጼዎቹ ቤት ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆየውን ውል እንዳራዘመ ለማወቅ ተችሏል ።

ሀብታሙ ተከሰተ በፋሲል ቤት ከ ሱራፌል ዳኛቸው ፣ ያሬድ ባየህ እና ከድር ኩሊባሊ በመቀጠል ውሉን ያራዘመ ተጫዋች ለመሆን ችሏል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor