መነሻ ገጽ ሪፖርት ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ደረጃውን ከፍ አደረገ።
ሪፖርትኢትዮጵያ ቡናየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግፋሲል ከተማ

ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን በማሸነፍ ደረጃውን ከፍ አደረገ።

አጋራ
አጋራ

በ 8ተኛው ሳምንት እሁድ በተደረገ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ጎንደር ላይ ፋሲል ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ በጠባብ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።ባለ ሜዳዎቹ አፄዎቹ ወደ ወላይታ አቅንቶ ባለቀ ሰዓት በተገኘ ፍፁም ቅጣት ምት አግኝቶ አቻ ወጥቶ ከተመለሰው ስብስባቸው የ አንድ ተጨዋች ቅያሪ በማድረግ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት በአንፃሩ እንግዳው ቡድን ኢትዮጲያ ቡና የሁለት ተጨዋች ቅያሬ በማድረግ ነበር ወደ ሜዳ የገቡት፡፡

ከአፄዎቹ የደጋፊ ማህበር ለክለቡ ድጋፋ ላደረጉ ባለውለተኞች የምስክር ወረቀት በመስጠት ነበር ጨዋታው የተጀመረው፡፡

በተለመደው እና በሁለቱም ደጋፊዋች በኩል የታየው ውብ የደጋፊዎች ዝማሬ ና የስታዲየም ድባብ የጀመረው ጨዋታው ኢትዮጵያ ቡናዎች በጉዳት ወሳኝ የመስመር አጥቂያቸውን አቡበከር ነስሩን በጨዋታው የመጀመርያ ደቂቃዎች ላይ ባስተናገደው ጉዳት በአላዛር ሽመልስ ለመቀየር ተገደዋል።

በመጀመሪያው አጋማሽ ኢትዮጵያ ቡናዎች ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ ኳስ መቆጣጠር ችለዋል ቢሆንም አልበገር ያለውን የአፄዎቹን የፊት መስመር የመልሶ ማጥቃት ማስቆም አልቻሉም፡፡

በዚህም በ10ኛው ደቂቃ ከኢትዮጵያ ቡናዎች የተከላካይ መስመር በተገኘ ስህተት ከሱራፌል ዳኛቸው ያገኘውን ኳስ ልማደኛው የጎል አነፍናፊ ሙጅብ ቃሲም ለፋሲል ከነማ ጎል ማስቆጠር ችሏል።

ከጎሏ መቆጠር በኋላ ወደ ኋላ አፈግፍገው መጫወት የመረጡት ፋሲል ከነማዎች ለካሳዬ አራጌ ቡድን አጨዋወት ምቹ ሆነዋል፡፡በአንፃሩ ፋሲል ከነማዎች ወደ ኋላ በማፈግፈግ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወት ሞክረዋል፡፡ከሱራፌል ዳኛቸው የሚጣሉትን ኳሶች አደገኛ መሆናቸው በዛሬው ጨዋታም ማስተዋል ችለናል።

የመጀመሪያው አጋማሽ በኢትዮጵያ ቡና የኳስ ቁጥጥር ና በፋሲል ከነማ የጎል መሪነት ተጠናቋል፡፡

በሁለተኛው አጋማሽም ተመጣጣኝ ሙከራ ቢያሳዩንም የካሳዬ አራጌ ቡድን በኳስ ቁጥጥሩ የተሻለ ነበር።

በዚህም የተነሳ በሰባ ስምንተኛው ደቂቃ ሀብታሙ ታደሰ ከአማኑኤል ዮሀንስ የተሻገረለትን ኳስ በግሩም ሁኔታ የሳማኪ መረብ ላይ አሳርፏታል።

ከጎሏ መቆጠር በኋላ ፋሲል ከነማዎች በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ቡናዎች የግብ ክልል ሲደርሱ ተስተውለናል፡፡በዚህም የተነሳ በሰማንያ አምስተኝው ደቂቃ ሱራፌል ዳኛቸው ከማዕዘን ምት ያሻገረለትን ኳስ በዚህ አመት ድንቅ ጊዜ እያሳለፈ የሚገኘው አጥቂው ሙጂብ ቃሲም ድንቅ የግምባር ኳስ አስቆጥሯል፡፡ጨዋታውም በዚሁ ውጤት መጠናቀቅ ችሏል።

ውጤቱን ተከትሎ ፋሲል ከነማ ነጥቡን ወደ 15 በማሳደግ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በአንፃሩ እንግዳው ቡድን ኢትዮጵያ ቡና ዘጠኝ ነጥብ በመያዝ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ፎቶ ክሬዲት (የሙጂብ ቃሲም) : አሌክስ ፎቶ

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

አዳማ ከአስር ፈረሰኞቹ ከሦስት እና ነብሮቹ ከአራት ጨዋታዎች በኋላ አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የመክፈቻ ቀን ጨዋታ አዳማ ከተማ በጎል ደምቆ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ...

ዜናዎችየአዲስአበባ እግርኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጠዋል የተባሉት ሁለት ዳኞች ወደ መጡበት እንዲመለሱ ተደረገ

በዮሴፍ ከፈለኝ በወልዋሎ እና ነገሌ አርሲ ጨዋታ ላይ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ ሁለት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ30ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች መናፍ ዐወል (አዳማ ከተማ): ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...