ፋሲል ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅጣት ተላለፈባቸው

 

ሁለቱም ክለቦች ቅጣቱ የተላለፈባቸው በ14ኛ ሳምንት በተደረገው የሁለቱም ቡድኖች ባደረጉት ጨወታ በደጋፊዎች መሀል ረብሺ ነበራቹህ ሲል ነው የቀጣቸው።

የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሁለቱ ክለቦች ጎንደር ላይ ባደረጉት ጨዋታ የተነሳውን ረብሻ ተከትሎ የቀረበውን ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ ቅጣት አስተላልፏል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ጊዮርጊስም ሆነ ፋሲል ከነማ ቀይና ቢጫ ካርድ ባዩት ተጨዋቾቻቸው ምክንያት አምስት አምስት ሺህ ብር እንዲከፍሉ ሲወሰን። ከዚህ በተጨማሪ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ዳኞቹ ላይ በመታፋት በመሳደብ ለድብደባ ሙከራ በማድረግ እንዲሁም ዳኞቹ ከሜዳ እንዳይወጡ በማድረግ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ ዳኞቹም በፓትሮል ታጅበው የወጡት ከ20 ደቂቃ እገታ በኋላ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል። በዚህም አንድ ጨዋታ በገለልተኛ ሜዳ እንዲጫወቱና አወዳዳሪው አካል ሜዳውን እንዲመርጥ የ30 ሺህ ብር እንዲከፍሉም ወስኗል፡፡

ይህንን የገንዘብ ቅጣት በ7 ቀን ውስጥ እንዲከፍሉ ካልከፈሉ የቅጣቱ 2% በየቀኑ እንደሚጨምር በማስጠንቀቅ ይህ የማይሆን ከሆነ ከፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ምንም አይነት ግልጋሎት እንዳያገኙ መወሰኑ ተረጋግጧል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport