ፊሊፕ ኦቮኖ ለኢኳቶሪያል ጊኒ ክለብ ፊርማውን አኖረ
ያለፉትን ዓመታት በመቐለ 70 እንደርታ አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ በመባል የተመረጠው ፍሊፕ ኦቮኖ በይፋ ከደቂቃዎች በፊት ፉትሮ ከንግስን መቀላቀል ችሏል ።
ኢኳቶሪያል ጊኒያዊው የመቐለ 70 እንደርታ ግብ ጠባቂ ከሀገራችን አራት ክለቦች ጥያቄዎች የቀረቡለት ቢሆንም ከስምምነት መድረስ አለማቻሉን የሰርነስ ሶከር ኤጀንሲ እና የተጫዋቹ ወኪል አቶ ሳምሶን ነስሮ ገልፀዋል ።
ፍሊፕ ኦቮኖ በተለይም ፊርማውን ገና ትናንት ማምሻውን ማኖሩን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ወደ ሀገሩ ሳያቀና በተለያዩ ሚዲያዎች የተሰሩበት ዜናዎች ሊያደርጋቸው አስቧቸው ለነበሩት ዝውውሮች ስንክሳር እንደነበረበት እና እንዳሳዘነው ለማወቅ ችለናል ።
የ 27 ዓመቱ ግብ ጠባቂ ፍሊፕ ኦቮኖ በቀጣዪ የውድድር ዓመት የካፍ ሻምፒንስ ሊግ ውድድር የፉትሮ ኪንግስን መረብ በመጠበቅ የሚወዳደር ይሆናል ።
ፍሊፕ ኦቮኖ የክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ ከመሆኑ በላይ የሀገሪቱን የዝውውር ሪከርድ በመስበር ክለቡን ሲቀላቀል በፉትሮ ኪንግስ የቤት ፣ መኪና እንዲሁም ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በኮንትራቱ ላይ መካተቱን አቶ ሳምሶን ገልፀውልናል ።