ነገ በ17ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ መርሃ ግብር ፈረሰኞቹ ከ አፄዎቹ የሚያደርጉት ጨዋታ ያለ ተመልካች በዝግ ስታዲዬም ይካሄዳል በሚል ደጋፊዎች ስጋት ቢገባቸውም ጨዋታው በደጋፊዎች ታጅቦ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
በ14ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚዬር ሊግ የካቲት 8 ቀን 2010 ዓ/ም በአዲስአበባ ስታዲዬም ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአዳማ ከነማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ ደጋፊዎች ያልተገባ ስፖርታዊ ጨዋነት አሳይተዋል በሚል የእግር ኳስ የፌደሬሽኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ በቅዱስጊዬርጊስ ስፖርት ክለብ ላይ 180,000 (አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ብር) ቅጣት እና 1 ጨዋታ በዝግ ስታዲዬም እንዲያደርግ ቅጣት መተላለፉ ይታወሳል፡፡
በመሆኑም የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር ይህንን ተከትሎ ለፌደሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ይግባኝ በማቅረቡ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ይግባኙን ተቀብሎ የቅጣት ውሳኔው ላይ ማሻሻያ በማድረግ ቅጣቱ ወደ 140,000 (አንድ መቶ አርባ ሺህ ብር) ዝቅ እንዲል እና 1 ጨዋታ በዝግ ስታዲዬም እንዲጫዎቱ የተወሰነው ቅጣትም በይግባኝ ሰሚ ኮሚቴው ውድቅ ሁኗል፡፡
በዚህ መሰረት ቅዱስ ጊዮርጊስ በ17ኛ ሳምንት መርኃ ግብር በነገው ዕለት ከፋሲል ከነማ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በተመልካች ታጅቦ የሚካሄድ ይሆናል፡፡
አስተያየት ይስጡ