ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲን ከሜዳው ውጪ በሰፊ የግብ ልዩነት በማሸነፍ ለአንድ ቀን በፋሲል ከነማ ተነጥቆ የነበረውን መሪነት መልሶ ተረክቧል፤ ቡድኑ የእሁዱን
ጨዋታ ሲያሸንፍም አጥቂዎቹ ጌታነህ ከበደ እና አቤል ያለው ሁለት ሁለት የድል ጎሎችን ያስቆጠሩ ሲሆን ይህ ከሜዳ ውጪ የተመዘገበ የድል ውጤትም ለቡድኑም ዘንድሮ የመጀመሪያ
ሆኖም ተመዝግቧል፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን መሪነት በያዘበት በአሁን ሰዓት ተከታዩን ፋሲል ከነማን በአንድ ነጥብ ልዩነት የሚበልጠው ሲሆን ሁለቱ ክለቦች በሳምንቱ መጨረሻ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ
በሁሉም ዘንድ በጉጉት እየተጠበቀ ይገኛል፤ ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሳምንቱ መጨረሻ ቀን ድ7370
7ል፤ ስለመሪነታቸው፣ ከፋሲል ከነማ ጋር ስለሚያደርጉት ጨዋታና ስለራሱ በአሁን ሰዓት ለክለቡ
ጥሩ እንቅስቃሴ በማሳየት ላይ የሚገኘውን የቡድኑን ተጨዋች ደስታ ደሙን ጋዜጠኛ መሸሻ ወልዴ ጠይቆት በሚከተለው መልኩ ምላሽ ሰጥቶታል፡፡
ሀትሪክ፡- ቅ/ጊዮርጊስ 4 ወልዋሎ አዲግ ራት 1 የሚል ውጤት በሳምንቱ የመ ጨረሻ ቀናት ተመዘገበና መሪነቱን መልሳችሁ ጨበጣ ችሁ፤ ካስቆጠራችሁት የግብ ብዛት አኳያ ግጥሚያው
ቀሏችሁ ነበር ማለት ይቻላል?
ደስታ፡- በፍፁም፤ ወልዋሎ አዲግራት ላይ አራት ግቦችን አስቆጥረን አሸነፍን እንጂ ጨዋታው ለእኛ በጣም ከባድ ነበር፤ ያም ሆኖ ግን እኛ ያገኘናቸውን የግብ ዕድሎች እና
አጋጣሚዎችን በአግባቡ ልንጠቀም ስለቻልን ጨዋታውን ማሸነፍ ችለናል፡፡
ሀትሪክ፡- ወልዋሎን ስታሸንፉ የነበራችሁ ጠንካራ ጎን ምን ነበር?
ደስታ፡- ጠንካራው ጎናችን ከዕለት ወደ ዕለት ስንጓዝ ያለን የቡድንና የአሸናፊነት መንፈሳችን ጥሩ መሆን መቻሉ ነው፤ ከዛ በተጨማሪም ወደፊት ተጭነን ስንጫወትም በጋራ ተጋግዘን
ስለሆነ ያ ለየት ያደርገናል፤ ውጤታማም እያደረገን ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደ ቡድን ያለበት ክፍተት ምንድን ነው?
ደስታ፡- ብዙም ክፍተት አለብን ብዬ አላስብም፤ የሚቀሩን ነገሮች ግን አሉ፡፡
ሀትሪክ፡- እነዛ ምንድን ናቸው?
ደስታ፡- የመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች ላይ ወደ ሜዳ ስንገባ መነሳሳት ላይ ይቀረን ነበር እሱን እያስተካከልን እንገኛለን፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ በምርጥ ብቃቱ ላይ ነው የሚገኘው?
ደስታ፡- ሙሉ ለሙሉ እንደዛ ለማለት ባያስደፍርም አዎን ጥሩ ነን፡፡
ሀትሪክ፡- ከሜዳ ውጪ ማሸነፍ የተለየ የደስታ ስሜት ይሰጣል?
ደስታ፡- በሚገባ፤ ምክንያቱም ብዙ ቡድኖች ይህን እድል እያገኙ አይደለምና፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ፋሲል ከነማ፣ መቐለ 70 እንደርታ ከሜዳ ውጪ ያሸነፉ ክለቦች ሆነዋል፤ ሌሎቹ ግን ማሸነፍን አልቻሉም….?
ደስታ፡- ማንኛውም ቡድን ጠንክሮና በርትቶ ከሰራ ከሜዳው ውጪ ያለውን ጨዋታ ማሸነፍ እንደሚችል እኛን ጨምሮ ያሳየን ክለቦች አለን፤ እሁድ እኛ ቅዳሜ ደግሞ ፋሲል ከነማ ይህን
አሳክተዋል፡፡
ሀትሪክ፡- ቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን በያዘው መሪነት ይቀጥላል፤ የውድድሩ ሻምፒዮናስ ይሆናል?
ደስታ፡- በእርግጠኝነት ነው የምነግርህ፤ መሪነታችን ይቀጥላል፤ ሻምፒዮናነታችንም እውን ይሆናል፡፡
ሀትሪክ፡- ከፋሲል ከነማ ጋር ወሳኝና ተጠባቂውን ጨዋታ የፊታችን እሁድ ጎንደር ላይ ታደርጋላችሁ፤ በሁለታችሁ መካከል ምን አይነት ፉክክር ይኖራል? ማንስ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል?
- ማሰታውቂያ -
ደስታ፡- ከፋሲል ከነማ ጋር የምናደርገው ጨዋታ ሁለታችን ካለን የነጥብ ቅርርብ አኳያ እኛ ካሸነፍን የነጥብ ልዩነቱን በመ ጠኑ የምናሰፋበት እነሱ ካሸነፉ ደግሞ መሪ የሚሆኑበት ሁኔታ
ስላለ በሁለታችን ክለቦች መካከል የሚኖረው ጨዋታ የዋንጫ ያህል ነው፤ ጥሩ ፉክክርም ይታይበታል፤ ጨዋታው ምንም እንኳን ጎንደር ላይ የሚካሄድና ለእኛም ከባድ የሚሆንብን
ቢሆንም በመጨረሻ ግን የግጥሚያው አሸናፊ የምንሆነው እኛ ነን፡፡
ሀትሪክ፡- የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ጌታነህ ከበደ እና አቤል ያለው ጥምረት ምርጥ ነው ማለት ይቻላል?
ደስታ፡- አዎን፤ በጣም ምርጥ ጥምረት ነው ያላቸው፤ ይሄንን በሰሞኑ ጨዋታዎቻቸውም ላይ አሳይተዋል፤ በጋራ ተግባብተው ሲጫወቱ ደስ ይላሉምና ይሄንንም ይቀጥሉበታል፡፡
ሀትሪክ፡- አንተን ጨምሮ የደደቢት የቀድሞ ተጨዋቾች የአሁኑ ክለባቸውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ውጤታማ እያደረጉት ነው ይባላል?
ደስታ፡- የእውነት ነው፤ ለደደቢት የተጫ ወትን የቀድሞ ተጨዋቾች አጋጣሚው አገናኝቶን ቅዱስ ጊዮርጊስን በአሁን ሰዓት እየጠቀምነውና ውጤታማ እያደረግነው ይገ ኛል፤ ግን እኛ ብቻ
አይደለንም ሁሉም የቡድኑ ተጨዋች ጭምርም ነው ክለቡን ስኬታማ እያደረገው የሚገኘው፡፡
ሀትሪክ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ አሁን ቋሚ ተሰላፊ ብትሆንም መጀመሪያ ግን ተጠባባቂ ነበርክ ያኔ ስሜትህ ተጎድቶ ነበር?
ደስታ፡- በዛን ወቅት መጫወት ፍላጎቴ ቢሆንም፤ መሰለፍ እና አለመሰለፍ ደግሞ የአሰልጣኝ ውሳኔ ቢሆንም በፍፁም ስሜቴ አልተጎዳም፤ ምንም አይነት ስሜትም አልተሰ ማኝም፤
ምክንያቱም መጀመሪያ ከእኔ መሰለፍ ይልቅ የክለቡን ውጤታማነት አስቀድማለውና፡፡
ሀትሪክ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ መሰለፍ ነበረብኝ ብለህ ታስብ ነበር?
ደስታ፡- ይሄ የአሰልጣኝ ውሳኔ ነው፤ ያም ሆኖ ግን በጊዜው ከጉዳትም ሆነ ከማንኛውም ነገር ነፃ ነበርኩና እሱ እስኪያሰልፈኝ ጊዜ ድረስ እየጠበቅኩ ነበር በኋላም ላይ ተሳካልኝ፡፡
ሀትሪክ፡- በአሁን ሰዓት በጥሩ ብቃት ላይ ነው የምትገኘው? ታምኖብህስ ነው እየተጫወትክ ያለኸው?
ደስታ፡- በአሰልጣኙ ስለታመነብኝማ ነው እየተጫወትኩ ያለሁት፤ ወቅታዊ ብቃቴን በተመለከተ የመጨረሻ ጫፍ ላይ ባልገኝም በምችለው አቅም ግን ለቡድኔ ጥሩ አግልጋሎትን
እየሰጠውኝ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ የአሁን ሰዓት ላይ የምትጫወትበት ቦታ ምንምንን ይጠይቃል? ያንን እያሟላ ነው?
ደስታ፡- በእዛ ቦታ ላይ ስትጫወት መመላለስ የግድ ስለሆነ ትንፋሽ ይጠይቃል፤ አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ለአጥቂዎችም ክሮሶችን እያደረግክ ኳሶችን ማቀበልም አለብህና እነዚ ህን ነው
የሚጠይቀው፤ አሁን በቦታው ለእኔ የሚቀሩኝ ነገሮች ቢኖሩም እነሱን እያስተካ ከልኩ ነው የሚገኘው፡፡
ሀትሪክ፡- ብዙዎች አንተን በመሀል ተከላካይነት ነበር የሚያውቁክ?
ደስታ፡- አዎን፤ ከዚህ በፊት በጠቀስከው ቦታ ላይ ነበር የምጫወተው፤ አሰልጣኝ ደግሞ ሁሌም እኔ ባልኩህ ቦታ ተጫወት ካለህ የእሱን ትህዛዝ ማክበር የግድ ስለሚል ባዘዘኝ ስፍራ
እየተጫወትኩ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- ከሙገር ክለብ ተጨዋችነትህ በኋላ በደደቢት እና በወልዋሎ አዲግራት ቡድኖች ውስጥ ተጫውተህ አሳልፈሃል፤ እነዛ ጊዜያቶች ለአንተ ምርጥ ነበሩ?
ደስታ፡- በጣም እንጂ! መቼም የማልረሳቸውም ናቸው፡፡
ሀትሪክ፡- ለደስታ የመጨረሻ ግቡ ተብሎ ቢጠየቅ ምላሹ ምንድን ነው የሚሆነው?
ደስታ፡- የመጀመሪያው አሁን ባለሁበት የቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን ውስጥ ሻምፒዮና መሆን መቻል ነው፤ ከዛ ሲቀጥል ደግሞ የፕሮፌሽናል ተጨዋችነት እድሉ ሲገኝ ያን ባሳካ በጣም ደስ
ይለኛል፡፡
ሀትሪክ፡- በእግር ኳሱ እዚህ ደረጃ ለመድረስህ እነማንን ታመሰግናለህ?
ደስታ፡- ከሙገር ክለብ ተጨዋችነቴ አንስቶ አሁን እስካለሁበት ደረጃ ድረስ ከእኔ ጎን ሆነው እኔን የሚያበረታቱኝ ሰዎች በጣም ብዙ ናቸው፤ የሁሉንም ስም መጥራት ገፃችሁን
ስለሚያጣብብ ሁሉንም ለማመስገን እፈልጋለው፡፡
ሀትሪክ፡- ከአውሮፓ ክለቦች የማን ደጋፊ ነህ?
ደስታ፡- የእንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድ ነዋ!
ሀትሪክ፡- ሊቨርፑል የእንግሊዝን ፕሪምየ ር ሊግ ዋንጫ ሊያነሳ ተቃርቧል፤ ምን ትላለህ ?
ደስታ፡- ምንም፤ እሱ የተረጋጋጠ ነገር ነው፤ ከአሁን በኋላ መቼም በ22 ነጥብ እየመራ ዋንጫውን አያነሳም ማለት አይቻ ልም፡፡
ሀትሪክ፡- የማንቸስተር ዩናይትድ አብዛ ኛው ደጋፊዎች ማለት ይቻላል ሊቨር ፑል የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ አይፈ ልጉም፤ አንተስ?
ደስታ፡- እኔም፤ እንደእነሱ አልፈልግም፤ ዋንጫውን ባይበላ ደስ ይለኝ ነበር፤ ግን ማግኘቱ የግድ እየሆነ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ውስጥ የተለያዩ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ደጋፊ አላችሁ፤ በእነሱ ዙሪያ ታወራላችሁ?
ደስታ፡- አዎን፤ አንድአንዴ ቁጭ ብለን በምንገናኝበት ሰዓት ስለ ቡድኖቹና ስለጨ ዋታው እንነጋገራለን፡፡
ሀትሪክ፡- የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በአንተ አንደበት ሲገለፁ?
ደስታ፡- እነሱን በቃላት ብቻ መግለፅ ከባድ ነው፤ በጣም የተለዩ ናቸው፡፡
ሀትሪክ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ መጫወት መቻል የተለየ ስሜት ይሰጣል?
ደስታ፡- አዎን፤ ክለቡ የሀገሪቱ ትልቅ ቡድን ከመሆኑ አኳያ ለእነሱ መጫወት መቻሉ በጣም ነው ስሜት ያለው፤ በተለይ ደግሞ ግጥሚያውን በምትመራበት ሰዓት ሁሉም ከጎንህ
ሆኖ በከፍተኛ የደስታ ድጋፍ ስለሚያበረታታ ያ ለየት እንዲሉ ያደርጋቸዋል፡፡
ሀትሪክ፡- ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስትጫወት መሸነፍ መቻል ፈፅሞ አይወደድም፤ ስታሸንፉና ስትሸነፉ ያለህ ስሜት ምንድን ነው የሚመስለው?
ደስታ፡- በእኛ ክለብ ውስጥ መሸነፍ የተለመደ ነገር አይደለምና ከላይ እንደገለፅከው አይወደድም፤ በኳስ ግን ማሸነፍ፣ መሸነፍ እና አቻ መውጣት የሚያጋጥም ነገር ነውና አንድ አንዴ
እነዛን ልትቀበል የግድ ይላል፡፡
ሀትሪክ፡- በመጨረሻ?
ደስታ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ማንም ተወዳዳሪ ክለብ ጠንክሮ ሰርቶ ይምጣ እንጂ ወደ ክልል ሄዶ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች አሸንፎ እና ውጤቱንም አስጠብቆ መምጣት
እንደሚቻል እኛን ጨምሮ አንድ አንድ ክለቦች ያሳየንበት አጋጣሚ አለና ይሄ ለሁሉም ትምህርትም ይሆናል፤ ከዚህ በኋላ ወደ ክልል ወጥቶ ማሸነፍ አይቻልም የሚለው ነገር ከተነሳም ያ
የስንፍና ምልክትም ነው፡፡