ጅማ አባ ጅፋር ለሁለት ተጫዋቾች የማስጠንቀቂያ ወረቀት ስጥቷል

 

ጅማ አባ ጅፋር ለሁለት የወጭ ዜጋ ተጫዋቾች አጥቂው ያኩቡ መሀመድ እና ግብ ጠባቂው ሙሀመድ ሙንታሪ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጥቷል።

 

በክረምት የዝውውር መስኮት ቡድኑን የተቀላቀሉት ተጫዋቾቹ ከለቡን በአቋም መውረድ ምክንያት በሚፈልጋቸው መንገድ እያገለገሉ አለመሆናቸውን ተከትሎ ነው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የደረሳቸው። ተጫዋቾቹ በቀጣይ አቋማቸውን የማያስተካክሉ ከሆነ ክለቡ አርምጃ እንደሚወስድ ነው ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው። አጥቂው ያኩቡ መሀመድ አራት ጨዋታዎችን በቋሚ አሰላለፍ ተካቶ ጨዋታውን ሲጀምር በሁለት ጨዋታዎች ደግሞ ተቀይሮ መግባት የቻለ ሲሆን ግብ ጠባቂው ሙሀመድ ሙንታሪ ደግሞ በሶስት ጨዋታዎች ብቻ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor