በ 21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማ አባጅፋር የወራጅ ስጋት ያለበትን ኢትዮ ኤሌክትሪክን አስተናግዶ 4-0 በሆነ ውጤት ድል ነስታል፡፡
እሁድ ከቀኑ በ 9፡00 ሰአት ሊጀመር መርሀ ግብር የተያዘለት ጨዋታ በፌደራል ዳኛ ይርጋለም ወ/ጊዮርጊስ 9፡04 ሲል የጀመረው ጨዋታ
በባለሜዳዎቹ ቀያይቹ ሠርጓጆች እነደወትሮው ሁሉ ሲዳማ ቡናን የገጠሙበትን 4-4-2 አሰላለፍ ይዘው ሲገቡ እንግዳው ቡድን ኤሌክትሪክ በአንፃሩ 4-3-3 አሰላለፍን መርጦ ተጫውቷል ፡፡
ወደጎል በመድረሱ በኩል ቅድሚያውን የወሰዱት በታፈሰ ተስፋዬ ፊት አውራሪነት የሚመሩት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ነበሩ፡፡
ሆኖም ግን ጨዋታውን ለማንበብ 10 ደቂቃዎችን ያህል የፈጀባቸው የገብረመድህን ሀይሌው ጅማ አባጅፋር
ገና በ 13ኛው ደቂቃ ላይ በቀኝ ክንፍ ግሩም እንቅስቃሴ እያደረ ከሚገኘው ሄኖክ አዱኛ የተሻማውን ኳስ በግብ ጠባቂው እና በተከላካይ አለመናበብ የተገኘችውን አጋጣሚ በመጠቀም ባለሜዳዎቹን አጥቂው ሳምሶን ቆልቻ መሪ ማድረግ ችሏል ፡፡
ሆኖም አቻነትን ፍለጋ የተንቀሳቀሱት ኤሌክትሪኮች ከደቂቃዎች በኃላ 2 አስደንጋጭ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል ፡፡በጅማ አባጅፋር በኩል በ21ኛው ደቂቃ ላይ በ አንድ ሁለት ቅብብል ወደጎል መድረስ የቻሉት የአባጅፋር ልጆች ከ አማካኙ ዮናስ ገረመው የተሻገረለትን ኳስ ኤልያስ አታሮ አምክኗታል፡፡
ጨዋታው በባለሜዳዎቹ የመሀል ሜዳ ብልጫ የተወሰደባቸው ኤሌክትሪኮች ስራ ሲበዛበት የዋለውን ካሉሻ አልሀሰንን መድከም ተከትሎ የጨዋታው ሚዛን ወደ ጅማ ሊያጋድል ችሏል።
እንዲሁም በ29ኛው እና በ31ኛው ደቂቃ ሳምሶን ቆልቻ እና ኦኪኪ አፎላቢ የሳቱት ኳስ አስቆጪ ነበር።
በኤሌክትሪክ በኩል ከመሀል እየተሳበ ወደ ግብ ክልል የሚደርሰው ካሉሻ አልሀሰን እና የእለቱ ጨራሽ አጥቂ የነበረው ታፈሰ ተስፋዬ የግብ ሙከራዎች አይዘነጉም ፡፡
በዚህ ሁኔታ የቀጠለው ጨዋታ መደበኛው ግማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ሊጠናቀቅ በባከኑ ደቂቃዎች ውስጥ በአባጅፋሩ አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ ላይ የተሰራውን ጥፋት ተከትሎ የተሰጠውን ፍፁም ቅጣት ምት እራሱ ኦኪኪ አፎላቢ ለክለቡ 2ኛውን ግብ አስቆጥሮ የግብ ልዩነቱን አስፍተው እረፍት ወጥተዋል፡፡

ከእረፍት መልስ መሉ በሙሉ ብልጫን የወሰዱት ቀያይ ሰርጓጆቹ የአባጅፋር ልጆች አማራጮችን በማስፋት የማጥቃት ሚዛኑን በቀኝ ክንፍ እንዲሁም በመሀል ከዮናስ ገረመው እና ይሁን እነደሻው የሚነሱትን ኳሶች 3ኛ ግብ ለማድረግ ደቂቃዎችን ወስዶባቸዋል ፡፡
በአንፃሩ ኤሌክትሪኮች
ተቀይሮ የገባው ጥላሁን ወልዴ ከታፈሰ ተስፋዬ ጋር በ አንድ ሁለት ቅብብል የሳቱት ኳስ እምታስቆጭ አጋጣሚ ነበረች ፡፡
በጨዋታው የወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪ የጅማ አባጅፋሩ ኦኪኪ ኦፎላቢ በተደጋጋሚ ወደ ግብ ቀርቦ ያመከናቸው ኳሶችም ተጠቃሽ ናቸው።
በ72ኛው ደቂቃ ላይ የአባጅፋሮች ፊት አውራሪው ኦኪኪ ኦፎላቢ ወደግቡ አክርሮ የመታውን ኳስ በተመለሰችበት ቅፅበት ተቀይሮ የገባው ተመስገን ገብረኪዳን በግሩም ቅልጥፍና ወደግብ ቀይሮታል።
ከዚህ ጎል መቆጠር በኀላ ተሽለው ለመጫወት የሞከሩት ኤሌክትሪኮች ኳሶች ከ ካሉሻ አልሀሰን በመደራጀት በታፈሰ ተስፋዬ እና ጥላሁን ወልዴ ግሩም ሙከራዎችን ማድረገ ችለዋል፡፡
ሆኖም የካሉሻን የኀላ ኀላ መዳከም ተከትሎ አባጅፋሮች በመልሶ ማጥቃት ወደ ፊት ለመድረስ ጥረት ሲያረጉ ተስተውሏል ፡፡
በዚህም የጨዋታ ሂደት የማታ ማታ መደበኛ 90 ደቂቃ ተጠናቆ ተጨማሪ 3 ደቂቃዎች ላይ ኦኪኪ ኦፎላቢ የግል ብቃቱን ተጠቅሞ ግሩም ጎል በማስቆጠር ለክለቡ 4ኛ ለራሱ ደግሞ 14ኛ ግቡን በማስቆጠር ጨዋታውን አሳርጓል፡፡
ይህን ተከትሎ ባለሜዳዎቹም የዚህ አመት ክስተቶች ባሉበት 1ኛ ደረጃ ላይ ረግተዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
አሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ – ጅማ አባጅፋር
“በመጀመሪያው 10 ደቂቃ የተጋጣሚያችንን አጨዋወት በማጥናታችን የተሳካ ስራ ሰርተናል። በውድድር ዓመቱ በጨዋታ ካስቆጠርናቸው ግቦች ከፍተኛው ነው።”
ም/አሰልጣኝ ቦጋለ ዘውዴ – ኤሌክትሪክ
“በጨዋታው ጅማአባጅፋሮች ሙሉ ለ ሙሉ የበላይነት ነበራቸው። በቀጣይ ቀሪ ጨዋታዎች ላይ ተጠናክረን እንመጣለን።”
አስተያየት ይስጡ