ጃኮ አረፋት ሰበታ ከተማን ለመቀላቀል ከጫፍ ሲደርስ አክሊሉ አየነው ወልዋሎ አ.ዩን ለሙከራ ተቀላቅሏል።

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የአንደኛ ዙር ተጠናቆ ተጫዋቾች እረፍት ላይ ቢሆኑም ክለቦች ግን በዝውውር ገበያው ላይ ተጠምደዋል። የካቲት 16 2012 ዓ.ም በጀመረው እና እስከ መጋቢት 16 2012 ዓ.ም በሚቆየው የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ክለቦች በርካታ ተጫዋቾችን እያስፈረሙ ይጠኛሉ።

በዚህ መሰረትም የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ፣ ወላይታ ድቻ፣ ባህር ዳር ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ አጥቂ የነበረው ጃኮ አረፋት አዲስ አዳጊውን እና በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሚያሰለጥነውን ሰበታ ከተማን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱን ሀትሪክ ስፖርት ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

በሌላ የዝውውር ዜና የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና እና የደደቢት የመሀል ተከላካይ የነበረው አክሊሉ አየነው ከወልዋሎ አ.ዩ. ጋር የሙከራ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል። አክሊሉ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ ክለብ መቆየቱ ይታወሳል።

hatricksport team

Hatricksport team

Facebook

hatricksport team

Hatricksport team