በዝውውር መስኮቱ የነቃ ተሳትፎን እያደረጉ የሚገኙት ድሬድዋ ከተማዎች ከደቂቃዎች በፊት የሰበታ ከተማውን የአማካይ ተከላካዩን ይስሐቅ መኩሪያን ማስፈረማቸው ታውቋል ፡፡

 

ይስሐቅ መኩሪያ በድሬድዋ ከተማ ቤት የሚያቆየውን የአንድ አመት ውል ሲፈራረም በቆየታው ለቡድኑ ትልቅ ሚናን እንደሚጫወት ሲጠበቅ ከእሱ በተጨማሪ በቦታው ተሰልፎ ክለቡን ለማገለገል ከዲሞክራቲክ ኮንጎው ፍሬድ ሙሹንዲ እና ከድር አዩብ ብርቱ ፉክክር እንደሚጠብቀው መገመት አያደዳግትም ።
ኢሳቅ መኩሪያ ከዚህ ቀደም በሰበታ ፤ ባህርዳር ከተማ ፤ ጅማ አባጅፋር እንዲሁም በፋሲል ከተማ መጫወት ችሏል ፡፡