ድሬዳዋ ከተማ ጋናውያን ተጫዋች አስፈርሟል።

 

በሁለተኛው ዙር እራሱን ለማጠናከር በንቃት እተሳተፈ ያለው ድሬዳዋ ከተማ የመሀል ተከላካዩ ክዌክ አንዶህ እና የአጥቂ መስመር ተጫዋቹ ፉሰይ ኑሁን አስፈርሟል።

የቀድሞ የመቐለ 70 እንደርታ ተጫዋች ፉሰይ ነይሁ ከደደቢት ከሳምንታት በፊት ከተለያየ በኋላ ወደ ቡርቱካናማዎቹን ተቀላቅሏል። ሌላኛው የክለቡ ፈራሚ የሆነው ክዌክ አንዶህ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር ተለያይቶ ወደ ወልቂጤ ያመራል ቢባልም ሳይሳካ ቀርቶ ወደ ድሬዳዋ አምርቷል። የሁለቱም ቡድን ተጫዋቾች የጤንነታቸው ሁኔታ በሚገባ የታየ ሲሆን በአንድ አመት የውል ኮንትራት ፊርማቸው ያኖሩ ሲሆን። የስራ ፍቃዳቸውን ጨርሰው ከሳምንት በኋላ ከቡድኑ ጋር ልምምድ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Hatricksport website Editor

Facebook

ሚሊዮን ኃይሌ

Hatricksport website Editor