ድሬዳዋ ከተማ የአራት ተጫዋቾችን ውል አራዘመ !

 

ድሬድዋ ከተማ የመስመር አጥቂ ቢንያም ጥዑመልሰን ፣ ግብ ጠባቂ ምንተስኖት የግሌ ፣ የፊት አጥቂ ሙየዲን ሙሳ እና የመስመር ተከላካይ ያሲን ጀማል ውል ማራዘማቸው ተሰምቷል ።

ቢንያም በ2010 ከናሽናል ሲሜንት ድሬድዋ ከተማን የተቀላቀለ ሲሆን አምና በመስመር አጥቂነት በመሰለፍ ክለቡን ማገልገል ችሏል። የቢንያም ኮንትራት ዘንድሮ የተጠናቀቀ ሲሆን አዲስ ለሁለት የሚያቆየውን ውል ፈርሟል።

ሌላው ውላቸውን ካሳደሱት ተጫዋቾች መካከል ግብ ጠባቂ ምንተስኖት የግሌ ሲሆን ምንተስኖትም ለሁለት አመት በክለቡ ለመቆየት ተስማምቷል።

ወደ ሐዲያ ሆሳና አምርቶ አምና ከተመለሰ በኃላ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው የፊት አጥቂው ሙየዲን ሙሳ ወይም በቅጽል ስሙ ክሪስ በመባል የሚታወቀው ለሁለት አመት በቡርትካናማዎቹ ቤት ለመቆየት ተስማምቷል።

አምና መስዋዕት በመክፈል የቡድኑን የመከላከል ስራ ሲያግዝ የነበረው ያሲን ጀማልም ሌላኛው አዲስ ውል የፈረመ ተጫዋች ነው ። የያሲን ኮንትራት በሚቀጥለው ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን ክለቡ ለተጨማሪ አንድ አመት ኮንትራቱን አራዝሞታል።

ድሬድዋ ከተማ የነባር ተጫዋቾችን ውል እያራዘመ ሲሆን አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ ይገኛል።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor