ዲሲፕሊን ኮሚቴ ወልቂጤ ከተማን ቀጥቷል

ወልቂጤ ከተማ በዲሲፕሊን ኮሚቴ ቅጣት ተላልፎበታል።

 

በ13ኛው ሳምንት መርሃግብር ወልቂጤ ከተማ ሲዳማ ቡናን ባስተናገደበት ለተከሰተው ስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል
ጥፋተኛ ነው በሚል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ወልቂጤ ከተማ 40ሺ ብር እንዲከፍልና 2 ጨዋታ ከሜዳ ውጪ እንዲጫወት ወስኗል፡፡

 

የገለልተኛ ሜዳውን አወዳዳሪው አካል እንዲወስን ገንዘቡን በ7 ቀን ገቢ እንዲያደርግ ካላደረገ በየቀኑ 2% በመቶ የሚጨምርና ካልከፈለም ማንኛውንም ግልጋሎት ከፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት እንዳያገኝ ተወስኗል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport