መነሻ ገጽ ዜናዎች ደደቢት እግርኳስ ክለብ ከኢሪያ የትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት ተፈራረመ 
ዜናዎችደደቢት

ደደቢት እግርኳስ ክለብ ከኢሪያ የትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት ተፈራረመ 

አጋራ
አጋራ

​ደደቢት እግር ኳስ ክለብ የጣሊያኑ የትጥቅ አምራች ኢርያ ምርት የሆነውን አዲሱን ትጥቅ ዛሬ በሞናርክ ሆቴል በይፋ አስተዋወቀ። 

ክለቡ ከኢሪያ ተወካይ ሚስተር ካርሎ ከደደቢት አስኪያጅ አቶ ሚኬኤሌ አምደመስቀል ጋር የሶስት አመት የማሊያ አቅርቦት እና ስፖንሰርሺፖ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
የትጥቅ ግዢው የደደቢት ዋና ማልያ እና ተለዋጭ ማልያን ያካተተ ሲሆን በተጨማሪም ልምምድ መስሪያ፣ የአሰልጣኞች ትጥቅ፣ ኳሶችን እና የመሳሰሉትንም ያካተተ ነው።

የስፓንሰር እና የትጥቅ አቅርቦት ስምምነቱ ለ 3ዓመት የሚቆይ ሲሆን ደደቢት በጥራት ተጠቃሚ ከመሆኑም ባሻገር በየዓመቱ ለትጥቅ ከሚያወጣው 50 በመቶ ማዳን ይችላል  በማለት የተናገሩት አቶ ሚኬኤሌ አምደመስቀል ናቸው፡፡
የጣሊያኑ የትጥቅ አምራች ኩባኒያ ኤሪያ ከትጥቅ ማቅረቡ በተጨማሪ ለደደቢት እግር ኳስ ክለብ  የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፎችን እንደሚያደርግ  በተወካዮ በሚስተር ካርሎ ተጠቅሷል ፡፡
በመጨረሻም የክለቡ የወንድ እና ሴት  ተጫዋቾች ማሊያውን በመልበስ ለጋዜጠኞች አስተዋውቀዋል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...