ደቡብ ሱዳን የወዳጅነት ጨዋታ ልታካሂድ ነው

 

ወደ እግር ኳሱ በቅርብ ዓመታት ብቅ በማለት አመርቂ ስራዎችን በመስራት ከዓመት ዓመት ተፎካካሪነታቸውን እያሳዩ የሚገኙት ጎረቤት ሀገር ደቡብ ሱዳን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያው ከዩጋንዳ ጋር ላለባቸው ጨዋታ መስከረም 30 የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያካሂዱ አሳውቀዋል ።

ደቡብ ሱዳኖች የወዳጅነት ጨዋታቸውን ከ 2017 የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊዋ ካሜሩን ጋር በያውንዴ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ ይፋ ተደርጓል ።

የደቡብ ሱዳን እግር ኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው ከካሜሩን የወዳጅነት ጨዋታ የቀረበላቸውን ጥያቄ መቀባላቸውን ሲያሳውቁ ከጨዋታው ስምንት ቀናት አስቀድመው በያውንዴ እንደሚከትሙ አሳውቀዋል ።

የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ቤሶንግ እንዳስታወቁት በቆይታቸው ከካሜሮን ሊግ ሀያላን ክለቦች እንደ ኮተን ስፖርት እንዲሁም የሊጉ ሻምፒዮን ባሜንዳም ጋር ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል ።

ከዚህ ቀደም ናይጄርያ ፣ ቱኒዚያ ፣ ኮትዲቯር፣ ኬፕ ቨርዴ እንዲሁም ሱዳን የወዳጅነት ጨዋታ እንደሚያካሂዱ ካሳወቁ ሀገራት መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor