የ2020 ሴቶች አፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ ድልድል ዛሬ ይፋ ማድረጉን ካፍ በላከው ደብዳቤ አሳውቋል። በዚህም መሰረት የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ሉሲዎቹ የመጀመሪያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከጅቡቲ አቻቸው ኢትዮጵያ ላይ የሚያከናውኑ ሲሆን የመልስ ጨዋታው ጅቡቲ ላይ ከመጋቢት 28 እስከ ሚያዝያ 6 ባሉ ቀናት እንደሚያከናውኑ አሳውቋል። ሁለተኛ ጨዋታቸውን ደግሞ ከሞሮኮ ብሄራዊ ቡድን ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 2 ባሉት ሁለት የተመረጡ ቀናት ያከናውናል። ማ፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ኢኳቴሪያል፣ጊኒ ፣ሞሮኮ፣ደቡብ አፍሪካ፣ ካሜሩን፣ ኮትዲቫር ያለቅድመ ማጣርያ በቀጥታ ምድብ ድልድል ውስጥ ማለፋቸው የአፍሪካ አግር ኳስ የበላይ አስተዳዳሪ ካፍ አሳውቋል።


አስተያየት ይስጡ