መነሻ ገጽ ዜናዎች የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የምድብ ድልድል በአክሲዮን ማህበር ምስረታ ወቅት በእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ይለያል::
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለቦች የምድብ ድልድል በአክሲዮን ማህበር ምስረታ ወቅት በእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ይለያል::

አጋራ
አጋራ

መስከረም 08/2012ዓ.ም አዲስ አበባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ2012ዓ.ም ጀምሮ የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በሊግ ካምፓኒ እዲመራ መወሰኑ ይታወቃል፡፡ የኢትዮ ፕሪሚየር ሊግ ካምፓኒ ምስረታ መስከረም 13 በስካይ ላይት ሆቴል 24ቱም የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ቡድኖች በተገኙበት በይፋ የሚመሰረት ሲሆን፤ ለዚህ ቅድመ ዝግጅት አስፈላጊ የሆኑ ዶክመንቶች ለክለቦቹ የተላኩ ሲሆን ፌዴሬሽኑ ባደረጋቸው ማጣራቶች ክለቦቹም ለመስከረም 13 ፕሮግራም አስፈላጊውን ዝግጅት በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መስከረም 5/2012ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ 24 ቡድኖች የሚካፈሉበት የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሁለት ምድብ አንደሚካሄድ እና ከስፖርታዊ ጨዋነት ጋር ተያይዞ ያሉ መልካም ጅምሮች በተሳካ ሁኔታ እስከሚጠናቀቁ ድረስ ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ ጊዛዊ መፍተሄ በማመቻቸት መቐለ 70 እንድርታ፤ ደደቢት፤ ስሁል ሽረ እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ በአንድ ምድብ እንዲሁም ባሕር ዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ በሌላኛው ምድብ እንዲሆኑ በተጨማሪም ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ዲቻ በተለያየ ምድብ እንደሚደረጉ ከተገለጸው ውጭ በአንዳንድ ሚዲያዎች ፌዴሬሽኑ በሁለት ምደብ የሚካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድልድል ይፋ እንዳደረገ ተገልጾ እየቀረበ ያለው መረጃ ከእውነት የራቀ እና የስፖርት ቤተሰቡን እያሳሳተ የሚገኝ መሆኑን ተገንዝበናል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከላይ ከተጠቀሱት 8 ክለቦች በስተቀር የተቀሩት 16 ክለቦች ምድብ ድልድል መስከረም 13 በስካይ ላይት ሆቴል በሚደረገው የሊግ ካምፓኒ አክሲዮን ምስረታ ፕሮግራም ላይ በእጣ ማውጣት ድልድላቸው ይፋ እንደሚደረግ እያሳወቀ፤ የሚዲያ አካላት ለህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ በማደረስ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በአክብሮት ይጠይቃል፡፡

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...