መነሻ ገጽ ዜናዎች የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ውድድር አመራር ዓብይ ኮሚቴ የሚመራ ይሆናል።
ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ውድድር አመራር ዓብይ ኮሚቴ የሚመራ ይሆናል።

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ውድድር አመራር አብይ ኮሚቴ 7 አባላት ያሉት አመራሮች በጥቆማ ተመርጠዋል።
1. መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ–ሰብሳቢ
2. አቶ እሸቱ ቢያድጎ
3. አቶ አንበሴ መገርሳ
4. ዶ/ር ከሳቴ ለገሰ –ም/ሰብሳቢ
5. አቶ አሰፋ ኦሲሶ
6. አቶ አንበሳው አውግቸው
7. አቶ መንግስቱ ሳሳሞ
የ2012ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በክለቦች የሚመራ ይሆናል፤ ራሳቸውን ችለው ወደ ካምፓኒነት እስኪመጡ ድረስ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ለፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራር ዓብይ ኮሚቴ የቢሮ እና የማቴሪያል የሚያደርግ ይሆናል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም የሰነድ ርክክብ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራር አብይ ኮሚቴ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያካሂዳል፤ የውድድር ደንቡን እና የዲሲፕሊን መመሪያውንም ለኮሚቴው ያስረክባል።

ውድድሩን የሚመሩ ንዑሳን ኮሚቴዎች በጥናቱ መሰረት የሚደራጁ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራር ዓብይ ኮሚቴ
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ” ኮሚቴው በድንብ እስኪደራጅ ድረስ ፌዴሬሽኑ ቢሮ ያመቻቻል፤ እንዲሁም ቴክኒካል እገዛዎች እና የቢሮ እቃዎችን እናሟላለን። ከክለቦች አሰያየም ጋር ያለውን የምዝገባ ሂደት ጨርሰን የምናስረክብ ይሆናል፤ ይህ ኮሚቴ በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝቶ ውድድር የሚመራበትን ጊዜ እንወስናለን። ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር የስራ አስፈጻሚ አባላትን እናመሰግናለን፤ የተሻለ የውድድር ዘመን እመኛለሁ።”

Via- EFF

 

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...