የ2012 ቶታል ግማሽ ማራቶን ትላንት በሀዋሳ ተካሄደ

 

9ኛው የሀዋሳ ግማሽ ማራቶን በሸሚዝ ምርት በአለም ላይ ከሚታወቀው እና በሀዋሳ ኢንደስትሪያል ፓርክ ውስጥ የሚገኘው ታል አፒራል የስያሜ ስፖንሰር ነው ትላንት ውድድሩ የተከናወነው።

ባለፈው አመት ከሰላም አኳያ ቡዙ ውጣ ውረዶችን ያሳለፈችው ሀዋሳ የ2012 ግማሽ ማራቶን ሩጫ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዶባታል። ሩጫው ከ21 ኪሎ ሜትር በተጨማሪ የ 7ኪሜ እና የህፃናት ሩጫ የውድድሩ አካል ነበሩ። ከጤና ሩጫ በተጨማሪም ውድድሩ በ 21ኪሜ እና 7ኪሜ ለበርካታ አትሌቶች የውድድር መድረክ ሆኗል። እንደ እ.ኢ.አ 2010 ላይ የጀመረው ይህ ውድድር ለተከታታይ 5 አመታት ቢካሄድም በሁኔታዎች አለመመቻቸት ለሁለት አመት ተቋርጦ የነበረ ቢሆንም በባለድርሻ አካላት ድርድር ነው ይህ ውድድር ትናንት ሊካሄድ የቻለው ተብሏል።

በወንዶች 21ኪሜ

ገብሬ ሮባ 01:02:43.794 በመግባት የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን። ደረሰ ኪንዳ በ01:02:48.816 ሁለተኛ። ቹቹ አበበ ደግሞ በ 01:02:59.808 ስአት በመግባት ከፈጣን ትራንዚት ማሰልጠኛ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል።

በተመሳሳይ 21ኪሜ ሴቶች

ደሚቱ ሀዋሳ 01:14:32.303 በመግባት ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ። ጌታዘሩ አትሌቲክስ ማሰልጠኛን ወክላ የተወዳደረችው ፀጋነሽ መኮንን እና ዝናሽ ጌታቸው 01:14:37.530 አና 01:14:42.303 በመግባት ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በ7ኪሜ ኤሊት ወንዶች አስናቀ ጥላሁን የውድድሩ አሸናፊ ሲሆን። ሳድያ አወል ደግሞ የሴቶች ኤሊት 7ኪሜ አሸናፊ ሆናለች።

Managing Editor at Hatricksport Website

FacebookTwitterGoogle+YouTube

ሙሴ ግርማይ

Managing Editor at Hatricksport Website