የፕርሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ ህጋዊ ፍቃድ አገኘ !

 

ከዚህ ቀደም በሊግ አወዳዳሪ ኮሚቴ ይመራ የነበረው የኢትዮጵያ ወንዶች ፕርሚየር ሊግ ከዚ በሃላ በፕርሚየር ሊግ ሼር ካምፓኒ እንደሚተዳደር ተገልፆል ::

የፕርሚየር ሊጉ አብይ ኮሚቴ ቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ በዛሬው የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአንደኛ ዙር ውድድር ግምገማ የመክፈቻ ንግግር ላይ እንዳሉት ሼር ካምፓኒው ህጋዊ ፍቃድ አግኝቶ ሰርተፍኬት እንደተሰጠው እና በአቶ ክፍሌ ሰይፈ ዋና ስራ አስኪያጅነት እንደሚመራ ገልፀዋል ::

ሼር ካምፓኒው የፋይናንስ ሀላፊ እና የካሸር አካውንታንት ሀላፊዎችን ወደ ፊት ይፋ እንደሚያደርግም ተናግረዋል ::

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor