መነሻ ገጽ ሀዲያ ሆሳዕና የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤ ከተማ ከሜዳው ውጪ አብዮ ኤርሳሞ ላይ ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል
ሀዲያ ሆሳዕናወልቂጤ ከተማዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የጨዋታ ዘገባ | ወልቂጤ ከተማ ከሜዳው ውጪ አብዮ ኤርሳሞ ላይ ጣፋጭ ድል አስመዝግቧል

አጋራ
አጋራ

 

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ አጋማሽ ሲደረጉ ወደ አብዮ ኤርሳሞ ስታዲየም የተጓዘው አዲስ አዳጊው ወልቂጤ ከተማ ሌላኛውን አዲስ አዳጊ ሀድያ ሆሳዕናን 2-1 በማሸነፍ ወርቃማ 3ነጥቦች ይዞ ተመልሷል።

እስከ 10ኛው ሳምንት በተካሄደዱ 80 ጨዋታዎች ከሜዳ ውጪ የተመዘገቡ ድሎች 11 ብቻ ሲሆኑ ዛሬ ደግሞ ወልቂጤ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳቸው ውጪ በማሸነፍ (የዚህ ዙር ባለሜዳ ኢትዮጵያ ቡና በመሆኑ) ቁጥሩን ወደ 13 ማድረስ ችለዋል። ይህም በ88 ጨዋታዎች መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በሊጉ ከሜዳ ውጪ ተጉዞ ማሸነፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማሳያ ነው።

በጨዋታው የመጀመሪያዎቹ 25 ደቂቃዎች በሁለቱም በኩል የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ ቢስተዋልም ከ25ኛው ደቂቃ በኋላ እንግዳዎቹ ክትፎዎቹ ተጭነው መጫወት የቻሉ ሲሆን፣ ግብ ለማግኘት ግን ረዘም ያለ ሰዓት ፈጅቶባቸዋል። ባለሜዳዎቹ ሀድያ ሆሳዕናዎችም አልፎ አልፎ ወደ ግብ ክልል ለመድረስ ጥረት አድርገዋል።

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የመጀመሪያውን ግብ ለማስተናገድ እስከ መጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ መጠበቅ ተገዷል። የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 2ደቂቃዎች ሲቀሩት 43ኛው ደቂቃ ላይ ሳዲቅ ሴቾ ግብ አስቆጥሮ ወልቂጤ ከተማዎችን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል። ሽኩቻ እና ተደጋጋሚ የዳኛ ፊሽካ በበዛበት በዚህ ጨዋታ ሌላ ግብ ሳይታከልበት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።

በሁለተኛው አጋማሽ ወልቂጤ ከተማዎች ውጤቱን ለማስጠበቅ እና አጋጣሚው ሲገኝ ደግሞ ሁለተኛ ግብ ለማግኘት በጥንቃቄ ሲጫወቱ ነብሮቹ በአንፃሩ አቻ ለመሆን ተጭነው ሲጫወቱ ታይተዋል። ሁለተኛው አጋማሽ እንደ መጀመሪያው አጋማሽ ሁሉ ሽኩቻ እና ተደጋጋሚ የዳኛ ፊሽካ የበዛበት ነበር። ይህንንም ተከትሎ 75ኛው ደቂቃ ላይ ነብሮቹ ያገኙትን ፍፁም ቅጣት ሄኖክ አርፊጮ ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል። ሆኖም ግን ይህ አቻ ውጤት መዝለቅ የቻለው ለ4ደቂቃዎች ብቻ ነበር። 79ኛው ደቂቃ ላይ አዳነ በላይነህ ለወልቂጤ ያስቆጠራት ግብ ክትፎዎቹ ከሜዳቸው ውጪ ጣፋጭ ድል እንዲያስመዘግቡ አስችሏቸዋል።

ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ በደጋፊዎች መካከል በተከሰተ ረብሻ ደጋፊዎች የተጎዱ ሲሆን አብዛኞቹ ደጋፊዎች ህክምና ተደርጎላቸዋል ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...