መነሻ ገጽ ቅድመ ዳሰሳ የጨዋታ ዳሰሳ | ጅማ አባጅፋር ከ ወልቂጤ ከነማ
ቅድመ ዳሰሳወልቂጤ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግጅማ አባጅፋር

የጨዋታ ዳሰሳ | ጅማ አባጅፋር ከ ወልቂጤ ከነማ

አጋራ
አጋራ

ጨዋታ: ጅማ አባጅፋር ከ ወልቂጤ ከተማ
የጨዋታ ቀን: ረቡዕ ታህሳስ 29/2012
የጨዋታ ሰዓት: 9:00
የጨዋታ አርቢትር: ፌደራል አርቢትር ኢሳያስ ታደሰ
ቦታ: ጅማ አባ ጅፋር ዩኒቨርስቲ ስታዲየም

በበአል ማግስት በሚደረገው የሰባተኛው ሳምንት የሊጉ መርሀ ግብር አንዱ ይህ ተጠባቂ ጨዋታ ሲሆን የአንድ ጨዋታ ማሸነፍ በነጥብ ተጠጋግተው ለሚገኙት ክለቦች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ለውጦችን ሲፈጥር ይስተዋላል።

በጅማ አዲሱ ስታዲየም በፌድራል አርቢተር ኢሳያስ ታደሰ መሪነት ጨዋታው የሚካሄድ ይሆናል።

በስድስት ሳምንታት ጉዞ ውስጥ በሊጉ 103 ጎሎች ሊቆጠሩ ችለዋል።

ጅማ አባ ጅፋር ያለፈውን የሊግ ጨዋታ በስድስተኛው ሳምንት ከሜዳው ውጪ ከብዙ አሰልቺ ጉዞ እና ከጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ጋር ተደማምሮ አንድ ነጥብ ይዞ መመለስ ችሏል።

ወልቂጤ ከነማዎች በበኩላቸው በሜዳቸው በሊጉ ማሸነፍ እየተቸገረ ከሚገኘው ስሑል ሽሬ ጋር አቻ ሲለያይ በሰባተኛው ሳምንት የሚካሄደው መርሀ ግብር በብዙ መልኩ ከወዲሁ ተጠባቂነት አግኝቷል።

ጅማ አባ ጅፋሮች በአዲሱ ስታዲየም ሽንፈት አላስተናገዱም ብሎም ከባዱን ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፍ ችለዋል።

ወልቂጤ ከነማ በሊጉ ካደረጉት ከሜዳ ውጪ የመጨረሻ ጨዋታ በሜዳው በቀላሉ ሶስት ነጥብ የማይጥለውን ወላይታ ድቻ በወጣት ተጫዋቻቸው ጫላ ተሺታ ጎል ማሸነፍ ችለዋል።

ወልቂጤ ከነማዎች ጥሩ የሚባል አጨዋወትን ይዘው መቅረብ ቢችሉም በጃኮ አራፋት የሚመራው የፊት መስምር አሁንም ክፍተቶች ሲታዩበት ለአሰልጣኝ ደግአረገ ይግዛው ሰፊ ስራዎችን ማድረግ እንዳለበት የሚጠቁም ነው።

ጅማ አባ ጅፋሮች በበኩላቸው በዚህ ሳምንትም ግብ ጠባቂያቸው ሰኢድ ሀብታሙ ዳግም የሚጠበቅ ነው። ቡድኑ በተደጋጋሚ በሚጠቃበት ወቅት አደገኛ ሙከራዎችን ከማዳን አልፎ ለቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ ምክንያት ሲሆን ይታያል።

ሁለቱም ቡድኖች በሊጉ ከባህር ዳር ከተማ በመቀጠል ምንም አይነት የግብ እዳ የሌለባቸው ቡድኖች ናቸው።

ወልቂጤ ከነማ ከሊጉ መሪ ፋሲል ከነማ በሶስት ነጥብ ሲርቅ ጅማ አባ ጅፋር በአራት ነጥቦች ብቻ እርቀው ይገኛሉ።

በጅማ አባጅፋር በኩል ረጅም ጊዜ ጉዳት ላይ የነበሩት ሄኖክ ገምቴሳ እና ብሩክ ገብረአብ በጉዳት የነገው ጨዋታ የሚያመልጣቸው ሲሆን በወልቂጤ ከተማ በኩል ደግሞ አዳነ አባይነህ፣ ፍፁም ተፈሪ እና ቶማስ ስምረቱ የማይኖሩ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...