መነሻ ገጽ አርባምንጭ ከተማ የጨዋታ ዳሰሳ | አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ
አርባምንጭ ከተማየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዳሰሳድሬዳዋ ከተማ

የጨዋታ ዳሰሳ | አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

አጋራ
አጋራ

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ 14 ሳምንት መርሀግብር ማክሰኞ ከሚደረጉ ሁለት ጨዋታወች መካከል አርባምንጭ ላይ በወራጅ ቀጠናው ላይ የሚገኙ ብድኖችን ሚያገናኝው ጨዋታ ከፍተኛ ትኩረትን አግኝቷል፡፡

ባለሜዳወቹ አርባምንጮች ካደረጓቸው ሁለት ጨዋታዎች በሜዳቸው አዳማ ከተማን በፀጋዬ አበራ ብቸኛ ግብ 1-0 ማሸነፍ ሲችሉ ወደ ሀዋሳ ተጉዘው ከሀዋሳ ከተማ ጋር በተመስገን ካስትሮ የአቻነት ግብ 1-1 በመውጣት ማግኝት ከሚገባቸው 6 ነጥብ 4 ነጥብ በመሰብሰብ ለዚህ ጨዋታ ስደርሱ፡፡

በአንፃሩ ድሬዳዋ ከተማ ካደረጋቸው 2 ጨዋታዎች በሜዳው በኢትዮጵያ ቡና 2-0 ሲሸነፍ ወደ አዲስአበባ ተጉዞ ከቅዱስጊዮርጊስ ጋር በኩዋሜ አትራም ጎል መምራት ቢችሉም አበባው ቡጣቆ ባገባት ግብ አቻ በመውጣት ማግኝት ከሚገባቸው 6 ነጥብ 1 ነጥብ ብቻ ማሳካት ችለዋል፡፡
በጥሩ መነቃቃት ላይ ሚገኙት አዞዎቹ ከወራጅ ከጠናው ለመውጣት በሜዳቸው እንደመሆኑ መጠን በደጋፊዎቻቸው በመታገዝ ሙሉ  3ነጥብ ለማግኝት ወደ ሜዳ የሚገቡ ስሆን ባለፉት ጨዋታዎች ጥሩ ሲንቀሳቀሱ በነበሩት ተመስገን ካስትሮ ና ፀጋዬ አበራ አማካኝነት የድሬን ተከላካይ ክፍል እደሚፈትኑ ይጠበቃል፡፡

ተጋባዡ ድሬ ከተማ ከሜዳቸው ውጪ እንደመሆኑ መጠን ነጥብ ተጋርቶ ለመወጣት መከላከል ላይ መሰረት ያደረገ አጫዋወት ስልት በመያዝ ወደ ሜዳ የሚገቡ ስሆን በተከላካዮቻቸው አማካኝነት በሚጨናገፉ ኳሶች  በመልሶ ማጥቃት እንደሚጫወቱ ይጠበቃል፡፡
የሁለቱን ጨዋታ የበለጠ ተጠባባቂ የሚያደርገው ሁለቱም ቡድኖች በወራጅ ቀጠናው ውስጥ በእኩል ነጥብ በጎል ክፍያ ተበላልጠው መቀመጣቸው ስሆን፡፡

አምና ሁለቱ ቡድኖች ተገናኝተው በድሬዳዋ ከተማ 2-0 አሸናፊነት መጠናቀቁ አይረሳም፡፡

አርባምንጭ ከተማ በኩል ወንድሜነህ ዘሪሁንና እና ወንደሰን ሚልኪያስ በጉዳት ለጨዋታው የማይደርሱ ሲሆን ገ/ሚካኤል ያዕቆብ ከቅጣት እንዲሁም ብርሀኑ አዳሙም ከጉዳት ለዛሬው ጨዋታ ይደርሳሉ፡፡

በድሬዳዋ በኩል ሀብታሙ ወልዴ እና ሳምሶን አሰፋ አሁንም ከረዥም ጊዜ ጉዳታቸው ያላገገሙ ሲሆን   እጁ ላይ ጉዳት የደረሰበት አህመድ ረሺድ ሙሉ ለሙሉ ባያገግምም በጨዋታው እንደሚሰለፍ ይጠበቃል።

ጨዋታው በፌደራል ዳኛ ሚካኤል አረአያ የሚመራ ይሆናል

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...